ሩዋንዳ በማርቡርግ ቫይረስ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን ገለጸች

ሰብስክራይብ
ሩዋንዳ በማርቡርግ ቫይረስ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን ገለጸች ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ 26 ሰዎች በማርቡርግ በሽታ መያዛቸውን የሩዋንዳ ጤና ሚኒስትር ሳቢን ንሳንዚማና አስታውቀዋል። የጤና አገልግሎት ሰራተኞች በተለይም በፅኑ ሕክምና ክፍሎች ውስጥ የሚያገለግሉት በብዛት በበሽታው እንደተጠቁ ተነግሯል። የዚህ ገዳይ ቫይረስ ምልክቶች ከባድ ራስ ምታት፣ ማስታወክ እና የጡንቻ እና የሆድ ህመም ናቸው። በ88% የሞት ምጣኔ ማርቡርግ ከኢቦላ ጋር የሚቀራረብ ሲሆን በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር በሚፈጠር የሰውነት ፈሳሽ ንክኪ ይተላለፋል። ንሳንዚማና አክለውም የበሽታውን ስርጭት ለመግታት በቫይረሱ ከየተያዙ ሰዎች ጋር ግንኙነት የነበራቸውን የመለየት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ገልጸዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0