የመስከረም 17 ምሽት አበይት የዓለም ጉዳዮች፦

ሰብስክራይብ
የመስከረም 17 ምሽት አበይት የዓለም ጉዳዮች፦ 🟠 የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባላት ጋር ባካሄዱት የስራ አፈጻጸም ስብሰባ በአቪዬሽን ኮምፕሌክስ ልማት ዙሪያ ተወያይተዋል። 🟠 ፑቲን የኒውክሌር መመሪያን ስለመለወጥ ያደረጉት ንግግር ተፅዕኖ እንዳሳደረ እና ዩናይትድ ስቴትስ ኪዬቭ ሩሲያ ውስጥ ዘልቃ ጥቃት እንድትፈጽሙ አልፈቀደችም ሲሉ የፈረንሳይ "አርበኞች" ፓርቲ መሪ ፍሎሪያን ፊሊፖት ተናገሩ። 🟠 ሃንጋሪ በዩክሬን ያለውን ግጭት ለመፍታት የደቡባዊ ዓለም "የሰላም ወዳጆች" የተሰኘውን ቡድን እንደምትቀላቀል የሃንጋሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፒተር ስዚጃርቶ ተናገሩ። 🟠 የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ዶናልድ ትራምፕ ከቮሎዲሚር ዜለንስኪ ጋር ባደረጉት ውይይት ምርጫውን ካሸነፉ ከሹመታቸው በፊት ለዩክሬን ግጭት "ጥሩ" መፍትሄ እንደሚያገኙ ገለጹ። 🟠 የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ለንግግር መድረክ ላይ ሲወጡ በርካታ ልዑካን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ አዳራሽን ለቀው ወጡ። 🟠 መስከረም 21 ስራቸውን የሚለቁት የኔቶ ዋና ፀሀፊ የንስ ስቶልተንበርግ በመጨረሻው ፅሁፋቸው ህብረቱ ወደፊት ከድንበሩ ውጭ ኦፕሬሽን ሊያካሂድ እንደሚችል ጠቆሙ።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0