ኢትዮጵያ የብሪክስ ማዕቀፍ በዓለም አቀፍ ተቋማት ፍትሀዊ ውክልና እንዲሰፍን ለማድረግ ጉልህ ሚና ይጠበቅበታል አለች

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የብሪክስ ማዕቀፍ በዓለም አቀፍ ተቋማት ፍትሀዊ ውክልና እንዲሰፍን ለማድረግ ጉልህ ሚና ይጠበቅበታል አለች የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አጽቀሥላሴ በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 79ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን በተካሄደው የብሪክስ አባል አገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ የተናገሩት ነው። አምባሳደር ታዬ በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር በዓለም አቀፍ ተቋማት አስተዳደርና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ፍትሀዊ ውክልና እና ተሰሚነት እንዲሰፍን በሚደረገው የማሻሻያ ጥረት የብሪክስ ማዕቀፍ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል የሚል ተስፋ እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል። የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ ቅድሚያ ለአፍሪካ ውክልና መስጠት እንደሚገባውም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የአፍሪካን አቋም እንደምታራምድ የገለጹት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለአፍሪካ ሕጋዊ ጥያቄ እና ታሪካዊ ኢ-ፍትዊነት ግማሽ ምላሽ ሊሰጠው አይገባም ብለዋል። ሚኒስትሩ ውክልናው መልከዓ ምድርን፣ የብሪክስን የጋራ ዕሴቶች እና በብሪክስ ማዕቀፍ አባል ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት እና የተመድን ቻርተር ባማከለ መልኩ መከናወን አለበት ሲሉ መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  አመልክቷል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0