የማሊ ቱዋሬግ አማፂያን ከዩክሬን ድጋፍ እንደሚያገኙ የቡድኑ ተወካይ ይፋ አደረገ

ሰብስክራይብ
የማሊ ቱዋሬግ አማፂያን ከዩክሬን ድጋፍ እንደሚያገኙ የቡድኑ ተወካይ ይፋ አደረገ "ከዩክሬን ጋር ረጅም እና የተለያየ ግንኙነት አለን። ከተለያዩ የዩክሬን ኤጀንሲዎች ጋር ኮሚኒኬት እናደርጋለን፤ ከመረጃ መጋራት ባለፈም ውይይት እናካሂዳለን" ሲል የአማፂው ጥምረት ሲኤስፒ-ዲፒኤ የውጭ ግንኙነት ምክትል ዋና ፀሀፊ አታዬ አግ ሞሃመድ ለፈረንሣይ ሚዲያ ተናግሯል። የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ከማሊ ጦር ጋር በተደረገ ውጊያ ጥቅም ላይ እንደዋሉ የሚያሳይ ማስረጃ የተገኘ ሲሆን የዩክሬን ባለስልጣናት በማሊ ኃይሎች ላይ በተሰነዘረው ጥቃት እጃቸው እንዳለበት ከዚህ በፊት አምነዋል። በቢላል አግ አቸሪፍ የሚመራው ሲኤስፒ-ዲፒኤ በምላሹ ዩክሬን በአፍሪካ ጠላቶቿን እንድትዋጋ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጿል። ማሊ እና ኒጀር ዩክሬን ለአሸባሪዎች ድጋፍ ታደርጋለች በማለት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን አቋርጠዋል። የማሊ የሽግግር መንግሥት ኪየቭን የሚደግፉ ሀገራትን ጨምሮ ለዓለም መንግሥታት ዩክሬን "ሽብርተኝነትን በይፋ ትደግፋለች" ሲል ያሳወቀ ሲሆን ማሊ "ለዩክሬን ድጋፍ መስጠት ለሽብርተኝነት ድጋፍ መስጠት ነው" ይብላ እንድታስብ አስገድዷታል ሲልም አመልክቷል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0