የሱዳን ጦር በአማፅያኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ላይ በካርቱም ከፍተኛ ጥቃት ከፈተ

ሰብስክራይብ
የሱዳን ጦር በአማፅያኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ላይ በካርቱም ከፍተኛ ጥቃት ከፈተ እሮብ ማለዳ ላይ የጀመረው ጥቃት በአማፂያኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ቁጥጥር ስር ባሉ በርካታ ቁልፍ ቦታዎች ላይ ያነጣጠረ ሲሆን በከተማው መሃል፣ ምዕራብ እና ደቡብ አካባቢዎች ግጭቶች እንደነበሩ የሀገሪቱ የዜና ኤጀንሲ ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል። ሰራዊቱ ከአጎራባች ኦምዱርማን ድልድይ አቋርጦ በከፊል በአርኤስኤፍ ቁጥጥር ስር ወደ ነበረው ካርቱም እንደገፋ ተገልጿል። ከካርቱም በስተደቡብ የሚገኘው የአርሞሬድ ጦር ክፍል አቅራቢያ እና በሰኔ ወር በአርኤስኤፍ ቁጥጥር ስር ገብቶ የነበረው አል-ኢስትሪታጂያ ዋና መሥሪያ ቤትን ጨምሮ ከተለያዩ ቦታዎች ጭስ ሲወጣ ታይቷል። በማዕከላዊ ካርቱም በአል-አራቢ ገበያ፣ በጦር ኃይሉ ጠቅላይ ዕዝ ዋና መሥሪያ ቤት እና ከካርቱም ባሕሪ በስተደቡብ በሚገኘው ሲግናል ጦር ክፍል አቅራቢያ ግጭት እና ጭስ እንደነበር ተዘግቧል። ጦር ኃይሉ በካርቱም ካደረገው ጥቃት በተጨማሪ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ጠንካራ ይዞታዎች ናቸው በሚባሉት በሴናር ግዛት ዋና ከተማ ሲንጋ የምድር ጥቃት እንዲሁም በምስራቅ ዳርፉር ግዛት ዋና ከተማ ኤል ዴይን የአየር ድብደባ አካሂዷል። የሰራዊቱ ጥቃት የሱዳን ጦር ረዳት ዋና አዛዥ ጄኔራል ያሲር አል-አታ አርኤስኤፍ እና አጋሮቹን ለማጥፋት የአየር እና የምድር ጥቃት እንደሚያካሂዱ ከተናገሩ በኋላ የመጣ ነው። እንደ ተመድ መረጃ ከሆነ በጦርነቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሲቪሎች የተገደሉ ሲሆን ከ11 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ደግሞ ተፈናቅለዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0