ሩሲያ እና ዚምባብዌ ከቪዛ ነጻ ጉዞ ስምምነት ህዳር ወር ላይ ለመፈራረም እንዳሰቡ ተገለጸ በሩሲያ እና ዚምባብዌ መካከል የመንገደኞች እንቅስቃሴን ለማሳደግ ያለመው ከቪዛ ነጻ የጉዞ ስምምነት አየተጤነ እንደሆነ እና በፈረንጆቹ ከህዳር 5 እስከ 7 በሞስኮ በሚካሄደው አምስተኛው የሁለትዮሽ የበይነ መንግሥታት ኮሚሽን ስብሰባ ላይ ሊፈረም እንደሚችል በዚምባብዌ የሩሲያ አምባሳደር ኒኮላይ ክራሲልኒኮቭ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ወደ ዚምባብዌ ለመግባት የሚያስችለው የአንድ ግዜ የመግቢያ ቪዛ በድንበር መተላለፊያ በ30 ዶላር ክፍያ ይገኛል። በሩሲያ እና ዚምባብዌ መካከል ያለው የመንገደኞች ፍሰት ውስን በሆነ የበረራ አማራጭ እና ከፍተኛ የቲኬት ዋጋ ዝቅተኛ ቢሆንም ዚምባብዌ የቱሪዝም መሠረተ ልማቶችን በማዳበር በተለይም በቪክቶሪያ ፏፏቴ የሩሲያን ቱሪስቶች ለመሳብ ፍላጎት አሳይታለች። ሩሲያ ከበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ጋር ቪዛን በጋራ ለመሰረዝ ፍላጎት እንዳላት ከዚህ በፊት ገልጻለች።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ሩሲያ እና ዚምባብዌ ከቪዛ ነጻ ጉዞ ስምምነት ህዳር ወር ላይ ለመፈራረም እንዳሰቡ ተገለጸ
ሩሲያ እና ዚምባብዌ ከቪዛ ነጻ ጉዞ ስምምነት ህዳር ወር ላይ ለመፈራረም እንዳሰቡ ተገለጸ
Sputnik አፍሪካ
ሩሲያ እና ዚምባብዌ ከቪዛ ነጻ ጉዞ ስምምነት ህዳር ወር ላይ ለመፈራረም እንዳሰቡ ተገለጸ በሩሲያ እና ዚምባብዌ መካከል የመንገደኞች እንቅስቃሴን ለማሳደግ ያለመው ከቪዛ ነጻ የጉዞ ስምምነት አየተጤነ እንደሆነ እና በፈረንጆቹ ከህዳር 5 እስከ 7 በሞስኮ... 26.09.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-09-26T13:58+0300
2024-09-26T13:58+0300
2024-09-26T14:04+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ሩሲያ እና ዚምባብዌ ከቪዛ ነጻ ጉዞ ስምምነት ህዳር ወር ላይ ለመፈራረም እንዳሰቡ ተገለጸ
13:58 26.09.2024 (የተሻሻለ: 14:04 26.09.2024)
ሰብስክራይብ