ቱርክ በዩክሬን ግጭት የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና የእህል ስምምነቱ እንዲታደስ ጥረቷን እንደምትቀጥል ቃል ገብታለች

ሰብስክራይብ
ቱርክ በዩክሬን ግጭት የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና የእህል ስምምነቱ እንዲታደስ ጥረቷን እንደምትቀጥል ቃል ገብታለች "ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን እንዳሉት ቱርክ ሽምግልናን ጨምሮ ፍትሃዊ እና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የሚረዱ እርምጃዎችን ለመውሰድ ዝግጁ መሆኗን ገልፀው የጥቁር ባህር እህል ኢኒሼቲቭን እንደገና ለማነቃቃት እና በዩክሬን እና በሩሲያ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ጥረቷን ትቀጥላለች ብለዋል። የቱርክ ፕሬዝዳንት በኒውዮርክ ከቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ረቡዕ ዕለት ባደረጉት ውይይት ዙሪያ የፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት አስተያየት ሰጥቷል። የጥቁር ባህር እህል ኢኒሼቲቭ፣ የዩክሬን እና የሩሲያ የግብርና ምርቶችን ደህንነቱ በመጠበቀ ወደ ውጭ መላክ የሚያስችል ሲሆን በተባበሩት መንግስታት እና በቱርክ ሸምጋይነት የተደረገው ስምምነት እ.አ.አ ሐምሌ 2023 ላይ ጊዜው አብቅቷል። የሩሲያ እህል እና ማዳበሪያን ወደ ውጭ መላክን ለማቀላጠፍ የስምምነቱ ድንጋጌዎችን መጣሱን በመጥቀስ ሩሲያ ተሳትፎዋን ለማራዘም ፈቃደኛ አልሆነችም።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0