የመስከረም 15 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦

ሰብስክራይብ
የመስከረም 15 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦🟠 የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ኒውዮርክ ገብተዋል።🟠 በሩሲያ ኩርስክ እና ቤልጎሮድ አካባቢዎች ሁለት የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች በአንድ ሌሊት ተመትተው መውደቃቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።🟠 የቺሊው ፕሬዝዳንት ገብርኤል ቦሪች ብራዚል እና ህንድ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት እስከ 2025 ባለው ጊዜ ውስጥ ቋሚ አባል እንዲሆኑ ጠይቀዋል።🟠 ሄዝቦላህ በቴል አቪቭ ከተማ ለተፈፀመው የሮኬት ጥቃት ሃላፊነቱን ወስዷል ፤ ጥቃቱ የተፈጸመው በሞሳድ የስለላ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት ላይ መሆኑን የንቅናቄው መግለጫ ገልጿል።🟠 የአሜሪካ የስለላ ድርጅት ፕሬዝዳታዊ እጩ ዶናልድ ትራምፕ " ከኢራን በኩል የግድያ ዛቻ " መኖሩን አስመልክቶ ማብራሪያ መሰጠቱን የምርጫ ዘመቻው ዋና ፅህፈት ቤት አስታወቋል።🟠 የዓለም አቀፉ የውቶሚክ ኢነርጂ ኃላፊ ራፋኤል ግሮሲ በሚቀጥሉት ሳምንታት በቴህራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ላይ ለመነጋገር  ኢራንን ለመጎብኘት ማሰባቸውን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0