እስራኤል ደቡብ ሊባኖስ ላይ በፈፀመችው ጥቃት 492 ሰዎች መሞታቸውን የሊባኖስ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የድንገተኛ አደጋ ማዕከል አስታውቋል

ሰብስክራይብ
እስራኤል ደቡብ ሊባኖስ ላይ በፈፀመችው ጥቃት 492 ሰዎች መሞታቸውን የሊባኖስ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የድንገተኛ አደጋ ማዕከል አስታውቋል"በጥቃቱ 35 ህጻናት እና 58 ሴቶችን ጨምሮ 492 ሰዎች ሲገደሉ 1,645 ቆስለዋል" ሲል መግለጫው ገልጿል። ቀደም ሲል ሰኞ እለት የእስራኤል መከላከያ ሃይል በሊባኖስ ንቅናቄ ሂዝቦላ ኢላማዎች ላይ ከፍተኛ ጥቃት እያደረሰ መሆኑን ተናግሯል።የእስራኤል የአየር ጥቃት መሰንዘር የጀመረው ባለፈው ሳምንት በሊባኖስ በገመድ አልባ መሳሪያዎች ፍንዳታ ከተከስተ በኋላ ነው። በይፋዊ መረጃዎች መሠረት በፍንዳታው 37 ሰዎች ሲሞቱ  ከ3,000 በላይ ሰዎች ደገሞ ቆስለዋል።ከማህበራዊ ድረ-ገጾች የወጡ ምስሎች በሊባኖስ በበካ ሸለቆ በደቡብ እና በሰሜን የእስራኤል ጥቃት ያስከተለውን ውጤት ያሳያል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0