በዩክሬን ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ እንዳይመጣ "ዋነኛዋ የሰላም ተቃዋሚ " ዩናይትድ ኪንግደም ናት ሲሉ በተመድ የሩሲያ ምክትል አምባሳደር ዲሚትሪ ፖሊያንስኪ ለስፑትኒክ ተናግረዋል

ሰብስክራይብ
  በዩክሬን ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ እንዳይመጣ "ዋነኛዋ የሰላም ተቃዋሚ " ዩናይትድ ኪንግደም ናት ሲሉ በተመድ የሩሲያ ምክትል አምባሳደር ዲሚትሪ ፖሊያንስኪ ለስፑትኒክ ተናግረዋል"በእርግጥ የዩናይትድ ኪንግደም ሚና በጣም ጎልህ ነው። አሁን የሰላም ዋነኛ ተቃዋሚዋ እርሷ ናት " ሲሉ ፖሊያንስኪ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 79ኛው ጉባኤ ላይ ተናግሯል። ሁሉንም የሰላም ጥረቶች ከሚያበላሹ ድርጊቶች ጀርባ ለንደን እንዳለችም አክለዋል።አምባሳደሩ እ.ኤ.አ በ2022 በቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ሳቢያ የከሸፈውን የኢስታንቡል  የሰላም ድርድር አስታውሰዋል። በዚያው ዓመት የጸደይ ወቅት ጦርነቱ ሊቆም ይችል ነበር ፤ ነገር ግን የዩክሬን ባለስልጣናት ከሩሲያ ጋር ምንም አይነት ስምምነት እንዳይፈርሙ እና በኪዬቭ ገለልተኝነት ላይ እንዳይደራደሩ እንዳደረጉ የዩክሬን ተደራዳሪ ቡድን አንድ አባል ለመገናኛ ብዙሃን ተናግሯል። ባለፈው ሳምንት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዩክሬን የመደራደር ፍላጎት ካላት ሩሲያ ይህን ሃሳብ እንደማትቃወም ገልጸው ውይይቱ ግን በኢስታንቡል በተደረሰው ስምምነት መሰረት እንደሚደረግ ተናግረዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0