እስራኤል በሊባኖስ የሂዝቦላ ኢላማዎች ላይ ከፍተኛ ጥቃት እየፈፀመች መሆኑን ገለፀች "የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት በአሁኑ ጊዜ በሊባኖስ የሂዝቦላህ አሸባሪ ድርጅት ንብረት በሆኑ የአሸባሪዎች ኢላማዎች ላይ ሰፊ ድብደባ እያካሄደ ነው" ሲል የእስራኤል ጦር በቴሌግራም ገልጿል።እ.አ.አ መስከረም 17 እና 18 በተለያዩ የሊባኖስ አካባቢዎች ፔጀርስ እና ዎኪ ቶኪዎችን ጨምሮ የመገናኛ መሳሪያዎች ፈንድተዋል። ይፋዊ በሆኑ መረጃዎች መሰረት 37 ሰዎች ሲገደሉ ከ 3,000 በላይ ሰዎት ቆስለዋል።በሺዎች የሚቆጠሩ መሳሪያዎች በአንድ ጊዜ እንዲፈነዱ ያደረገው ምን እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም። ሂዝቦላህ እና የሊባኖስ ባለስልጣናት ለዚህ ክስተት እስራኤልን ተጠያቂ አድርገዋል። የእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ግን ሀገሪቱ በድርጊቱ እጇ የለበትም ሲሉ አስተባብለዋል። የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ የሊባኖሱን ክስተት አስከፊ የሽብር ተግባር እና ትልቅ ግጭት ለመቀስቀስ የተደረገ ሙከራ ሲሉ ጠርተውታል።የእስራኤል ጦር ቀደም ሲል በጋዛ ሰርጥ ላይ በተደረገው ዘመቻ የተሳተፈውን 98ኛ ክፍለ ጦር ከሊባኖስ ጋር በሚያዋስነው ድንበር ላይ መልሶ አስፍራል። የእስራኤል አየር ሃይል እስራኤልን ለመምታት በተዘጋጁት የሂዝቦላህ ተቋማት እና የሚሳኤል ማስወንጨፊያዎች ላይ ከፍተኛ የቦምብ ድብደባ እያካሄደ ነው።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
እስራኤል በሊባኖስ የሂዝቦላ ኢላማዎች ላይ ከፍተኛ ጥቃት እየፈፀመች መሆኑን ገለፀች
እስራኤል በሊባኖስ የሂዝቦላ ኢላማዎች ላይ ከፍተኛ ጥቃት እየፈፀመች መሆኑን ገለፀች
Sputnik አፍሪካ
እስራኤል በሊባኖስ የሂዝቦላ ኢላማዎች ላይ ከፍተኛ ጥቃት እየፈፀመች መሆኑን ገለፀች "የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት በአሁኑ ጊዜ በሊባኖስ የሂዝቦላህ አሸባሪ ድርጅት ንብረት በሆኑ የአሸባሪዎች ኢላማዎች ላይ ሰፊ ድብደባ እያካሄደ ነው" ሲል የእስራኤል ጦር... 23.09.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-09-23T15:40+0300
2024-09-23T15:40+0300
2024-09-23T16:04+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
እስራኤል በሊባኖስ የሂዝቦላ ኢላማዎች ላይ ከፍተኛ ጥቃት እየፈፀመች መሆኑን ገለፀች
15:40 23.09.2024 (የተሻሻለ: 16:04 23.09.2024)
ሰብስክራይብ