የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የሄይቲን ተልዕኮ ወደ ተመድ ሰላም ማስከበር ዘመቻ ሊቀይሩት ነው

ሰብስክራይብ
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የሄይቲን ተልዕኮ ወደ ተመድ ሰላም ማስከበር ዘመቻ ሊቀይሩት ነውሩቶ በሄይቲ ለዓመታት ለዘለቀው የፖለቲካ አለመረጋጋት እና ለጅምላ መፈናቀል ምክንያት የሆነውን ከባድ የቡድን ዝርፊያን ችግር ለመቅረፍ ያለመውን እና ኬንያ የተሳተፈችበትን የመልቲ ናሽናል ሴኪዩሪቲ ድጋፍ (MSS) ተልዕኮን ሂደት ለመገምገም ሄይቲን ጎብኝተዋል።በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ለ12 ወራት የተፈቀደው የመልቲ ናሽናል ሴኪዩሪቲ  ተልዕኮ ስልጣን በጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ ያበቃል። "የመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ሊወስድ የሚፈልገው አቅጣጫ ከሆነ ተልእኮውን ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ለማሸጋገር በቀረበው ሀሳብ ላይ ምንም አይነት ችግር የለብንም "የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔን ተከትሎ ኬንያ በሰኔ እና በሐምሌ ወራት ወደ 400 የሚጠጉ የፖሊስ መኮንኖችን ወደ ፖርት ኦ-ፕሪንስ ማሰማራቷ ይታወቃል። ሩቶ በቀጣይ 600 መኮንኖችን የያዘ ቡድን ለማሰማራት ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን ጠቅሰዋል። ኬንያ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ለተልዕኮው ዝግጁ በመሆን፤ ለስምሪቱም አስፈላጊውን እገዛ ትጠብቃለች ብለዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0