ኮትዲቯር በኮኮዋ ዋጋ ላይ በትንሹ የ23% ጭማሪ ልታደርግ ነው

ሰብስክራይብ
ኮትዲቯር በኮኮዋ ዋጋ ላይ በትንሹ የ23% ጭማሪ ልታደርግ ነው የሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ተቆጣጣሪ የሆነው የኮትዲቯር ቡና እና ኮኮዋ ምክር ቤት ከጥቅምት ወር ጀምሮ ለሚሰበሰበው ምርት ለአንድ ኪሎግራም ኮኮዋ ከ3.15 እስከ 3.40 ዶላር የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ እያሰበ እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮችን ጠቅሰው መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የዋጋ ጭማሪው በጋና ካለው የኮኮዋ ዋጋ እንዲበልጥ ያደርገዋል። ይሁን እንጂ የመጨረሻው ውሳኔ የፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት ነው የተባለ ሲሆን እስካሁን በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም። በምዕራብ አፍሪካ ካለው ደካማ ምርት የተነሳ የታህሳስ የወደፊት ኮንትራቶች በኒውዮርክ በቶን ከ7,500 ዶላር በላይ በመገበያየት ላይ ይገኛሉ።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0