ኔዘርላንድስ በቅኝ ግዛት ዘመን የወሰደቻቸውን 288 የባህል ቅርሶች ለኢንዶኔዢያ ልትመልስ እንደሆነ ተገለጸ "ከኢንዶኔዥያ በቀረበላት ጥያቄ መሰረት ኔዘርላንድስ ከደች መንግሥት ስብስብ ውስጥ 288 ዕቃዎችን ወደ ኢንዶኔዢያ እየመለሰች ነው። እነዚህ ዕቃዎች በቅኝ አገዛዝ ጊዜ ወደ ኔዘርላንድስ የተወሰዱ እና ለኢንዶኔዥያ ባህላዊ ጠቀሜታ ያላቸው ናቸው" ሲል የኔዘርላንድስ የትምህርት፣ ባሕል እና ሳይንስ ሚኒስቴር አርብ እለት አስታውቋል። ኔዘርላንድስ አራት የሂንዱ-ቡድሂስት ቅርፃ ቅርጾችን እና 284 ቁሳቁሶችን ከፑፑታን ባዱንግ ስብስብ ትመልሳለች ሲልም አክሏል። ቅርሶቹ በአሁኑ ጊዜ የወረልድ ሙዚየም ስብስብ አካል ሲሆኑ አርብ ወደ ኢንዶኔዢያ እንደሚመለሱም መግለጫው አመልክቷል። ውሳኔው በሀገሪቱ የቅኝ ግዛት ግዜ ስብስቦች ኮሚቴ ምክረ ሃሳብ እና በቅኝ ግዛት ስብስቦች ብሔራዊ ፖሊሲ መሰረት እንደተደረሰ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ኔዘርላንድስ በቅኝ ግዛት ዘመን የወሰደቻቸውን 288 የባህል ቅርሶች ለኢንዶኔዢያ ልትመልስ እንደሆነ ተገለጸ
ኔዘርላንድስ በቅኝ ግዛት ዘመን የወሰደቻቸውን 288 የባህል ቅርሶች ለኢንዶኔዢያ ልትመልስ እንደሆነ ተገለጸ
Sputnik አፍሪካ
ኔዘርላንድስ በቅኝ ግዛት ዘመን የወሰደቻቸውን 288 የባህል ቅርሶች ለኢንዶኔዢያ ልትመልስ እንደሆነ ተገለጸ "ከኢንዶኔዥያ በቀረበላት ጥያቄ መሰረት ኔዘርላንድስ ከደች መንግሥት ስብስብ ውስጥ 288 ዕቃዎችን ወደ ኢንዶኔዢያ እየመለሰች ነው። እነዚህ... 21.09.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-09-21T15:55+0300
2024-09-21T15:55+0300
2024-09-21T16:04+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ኔዘርላንድስ በቅኝ ግዛት ዘመን የወሰደቻቸውን 288 የባህል ቅርሶች ለኢንዶኔዢያ ልትመልስ እንደሆነ ተገለጸ
15:55 21.09.2024 (የተሻሻለ: 16:04 21.09.2024)
ሰብስክራይብ