ኢትዮጵያ የማተራመስ ሙከራዎችን አስጠንቅቃ ለቀጠናዊ ትብብር ቁርጠኝነቷን ገለጸች "ኢትዮጵያ ቀጠናውን ለማተራመስ እንዲሁም የልማት ጥረቷን ለማደናቀፍ የሚደረጉ ሙከራዎችን በዝምታ አትመለከትም" ሲሉ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነብያት ጌታቸው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ በሰጥቶ መቀበል መርህ የጋራ ልማት እና ቀጠናዊ ውህደት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ለሚኖራት ጠንካራ ግንኙነት ቅድሚያ እንደምትሰጥም አብራርተዋል። ቃል አቀባዩ በቅርቡ በጎረቤት ሀገር የተወሰደ እርምጃን ያነሱ ሲሆን ኢትዮጵያ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና ከጠብ አጫሪ ንግግሮች ለመቆጠብ ቁርጠኛ መሆኗን ደግመው ተናግረዋል። ሆኖም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን የሚነኩ ድርጊቶችን በቅርበት እንደምትከታተልና ተገቢውን ምላሽ እንደምትሰጥም አሳስበዋል። የቃል አቀባዩ አስተያየት ከጎረቤት ሶማሊያ ጋር ከባህር በር ስምምነት ጋር በተያያዘ ውጥረት በነገሰበት ወቅት የመጣ ነው። አለመግባባቱ ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጋር የባህር በር ስምምነት ከተፈራረመች በኋላ የተፈጠረ ነው። እርምጃው የሶማሊያ መንግሥትን በከፍተኛው ያስቆጣ ሲሆን በሁለቱ ጎረቤቶች መካከል ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት እንዲፈጠር አድርጓል። በቱርክ አደራዳሪነት ሊካሄድ ስለነበረው 3ኛ ዙር የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ንግግር መራዘምን አስመልክተው አስተያየት የሰጡት ቃል አቀባዩ መስከረም 7 ሊካሄድ የነበረው ድርድር ከጳጉሜ 5 እስከ መስከረም 20 ከሚካሄደው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ጋር የጊዜ ሰሌዳ ግጭት በመፈጠሩ ለሌላ ጊዜ መተላለፉን አስታውቀዋል። ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ኢትዮጵያ የማተራመስ ሙከራዎችን አስጠንቅቃ ለቀጠናዊ ትብብር ቁርጠኝነቷን ገለጸች
ኢትዮጵያ የማተራመስ ሙከራዎችን አስጠንቅቃ ለቀጠናዊ ትብብር ቁርጠኝነቷን ገለጸች
Sputnik አፍሪካ
ኢትዮጵያ የማተራመስ ሙከራዎችን አስጠነቅቃ ለቀጠናዊ ትብብር ቁርጠኝነቷን ገለጸች "ኢትዮጵያ ቀጠናውን ለማተራመስ እንዲሁም የልማት ጥረቷን ለማደናቀፍ የሚደረጉ ሙከራዎችን በዝምታ አትመለከትም" ሲሉ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነብያት... 21.09.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-09-21T10:56+0300
2024-09-21T10:56+0300
2024-09-21T14:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий