የመስከረም 10 ምሽት ዓበይት የዓለም ጉዳዮች፦

ሰብስክራይብ
የመስከረም 10 ምሽት ዓበይት የዓለም ጉዳዮች፦ 🟠 ከሩሲያ ጋር በተያያዘ ታሪክ ለፖለቲካ ጥቅም ሲባል አላግባብ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው ሲሉ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከሩሲያ የፀጥታ ምክር ቤት አባላት ጋር የታሪክ አተረጓጎምን በተመለከተ ባደረጉት ውይይት ተናግረዋል። 🟠 እስራኤል ቤይሩትን ለመምታት እንዳሰበች ለአሜሪካ እንዳላሳወቀች ዋይት ሀውስ ገልጿል። በሊባኖስ ዋና ከተማ ደቡባዊ ዳርቻ በእስራኤል በደረሰው ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 8 ከፍ እንዳለ እና 59 ሰዎች መቁሰላቸውን የሊባኖስን የጤና ሚኒስቴር ጠቅሰው መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 🟠 ቴህራን ለሃማስ ከፍተኛ መሪ ኢስማኢል ሃኒዬ ግድያ “በቅርቡ” ለእስራኤል ምላሽ ትሰጣለች ሲሉ የኢራን ሐይማኖታዊ መሪ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ተናግረዋል። 🟠 የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ዶናልድ ትራምፕ ላይ የተደረገውን የግድያ ሙከራ ተከትሎ የከፍተኛ የመንግሥት ስልጣን እጩዎች ደህንነትን ለማጠናከር የቀረበውን ረቂቅ ህግ አፅድቋል። 🟠 የዳኑቤ ወንዝ ቡዳፔስት ውስጥ መጠኑን አልፎ በ24 ሰዓት ውስጥ 30 ሴንቲሜትር ገደማ የጨመረ ሲሆን በሀንጋሪ መዲና የወንዙ የጎርፍ ከፍታ ቅዳሜ ይጠበቃል።መረጃዎቹን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0