በአፍሪካ የመጀመሪያው የኤምፖክስ ክትባት ዘመቻ በሩዋንዳ ተጀመረ

ሰብስክራይብ
በአፍሪካ የመጀመሪያው የኤምፖክስ ክትባት ዘመቻ በሩዋንዳ ተጀመረእንደ የአፍሪካ ህብረት የጤና ኤጀንሲ መረጃ ከመስከረም 7 ጀምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኤምፖክስ ክትባቶች ተሰጥተዋል።እንዚህ የመጀመሪያ ክትባቶች ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጋር በሚያዋስኑ ሰባት ወረዳዎች መሰጠታቸው ተገልጿል።የክትባት ዘመቻው “የህክምና ባለሙያዎችን፣ ድንበር ተሻጋሪ ሰራተኞችን፣ በቱሪዝም ውስጥ የሚሰሩ ሰዎችን እና ሌሎች ከፍተኛ ስጋት ያለባቸው ቡድኖች ላይ ያነጣጠረ ነው” ሲል የሩዋንዳ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡የወረርሽኙ ማዕከል በሆነችው በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ክትባቱ በጥቅምት ወር እንደሚጀመር የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል ዋና ዳይሬክተር ዣን ካሴያ ተናግረዋል። "ኤምፖክስ በአፍሪካ አሁንም በቁጥጥር ስር አይደለም፤ አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ አሁንም በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጠር እየጨመረ ነው" ሲሉ ዣን ካሴያ ተናግረዋል።በኤምፖክስ የሚያዙ ሰዎች ቁጠር በዓለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ ባለበት ወቅት የሩሲያ የሸማቾች መብት ተቆጣጣሪ ሀገሪቱ በተዳከመ የፈንጣጣ ቫይረስ ላይ የተመሰረተ እና በበኤምፖክስ ላይ ውጤታማ የሆነ ኦርቶፖክስቫክ ክትባት እንዳላት ጠቁሟል። በሩስያ የሳይንስ ማእከል "ቬክተር" የዳበረው ክትባቱ በ2022 የተመዘገበ ሲሆን ደህንነቱ የተረጋገጠ እና የመከላከል አቅሙ ጠንካራ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0