የመስከረም 20 ረፋድ አበይት የዓለም ጉዳዮች፦ 🟠 በሩሲያ ቤልጎሮድ ክልል ስምንት የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች በአንድ ሌሊት እንደወደሙ እና አንድ ሚሳኤል በሩሲያ ኩርስክ ክልል ላይ መመታቱን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። 🟠 የሊባኖስ ነዋሪዎች ተጨማሪ ፍንዳታን በመፍራት ስልኮቻቸውን እና ሌሎች መሳሪያዎችን በማጥፋት ላይ መሆናቸውን የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 🟠 የእስራኤል አየር ኃይል በደቡባዊ ሊባኖስ ለሁለት ሰዓታት ባካሄደው ጥቃት ወደ 100 የሚጠጉ አስወንጫፊዎች እና ወታደራዊ ተቋማትን እንደመታ እንዲሁም 1,000 የሚደርሱ ተተኳሽ መሳርያዎች መውደማቸውን የእስራኤል ጦር አስታውቋል። 🟠 ሩሲያ በአርክቲክ ውቅያኖስ ላይ ያላትን ጥቅም በወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ እና ቴክኒካዊ መንገዶች ለማስጠበቅ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆኗን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ተናገሩ። 🟠 የዩናይትድ ስቴትስ ሚስጥራዊ የጥበቃ አገልግሎት አሜሪካዊው ስራ ፈጣሪ ኤለን መስክ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ እንደተካሄደው የግድያ ሙከራ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ላይም ሆነ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፕሬዝዳንታዊ እጩ ካማላ ሃሪስ ላይ አለመካሄዱ አስገርሞኛል ሲል በኤክስ (የቀድሞው ትዊተር) ገጹ ላይ አስፎሮ የሰረዘውን ጽሁፍ እየመረመረ እንደሆነ ገለጸ።መረጃዎቹን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የመስከረም 20 ረፋድ አበይት የዓለም ጉዳዮች፦
የመስከረም 20 ረፋድ አበይት የዓለም ጉዳዮች፦
Sputnik አፍሪካ
የመስከረም 20 ረፋድ አበይት የዓለም ጉዳዮች፦ 🟠 በሩሲያ ቤልጎሮድ ክልል ስምንት የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች በአንድ ሌሊት እንደወደሙ እና አንድ ሚሳኤል በሩሲያ ኩርስክ ክልል ላይ መመታቱን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። 🟠 የሊባኖስ... 20.09.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-09-20T13:09+0300
2024-09-20T13:09+0300
2024-09-20T13:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий