የፈረንሳይ ጦር ከ48 አመታት ቆይታ በኋላ ከኮትዲቯር ወታደራዊ ካምፕ ለቆ ወጣ

ሰብስክራይብ
የፈረንሳይ ጦር ከ48 አመታት ቆይታ በኋላ ከኮትዲቯር ወታደራዊ ካምፕ ለቆ ወጣ በሎሞ ኖርድ የሚገኘው የፈረንሳይ ጦር የተኩስ እና ወታደራዊ ልምምድ ካምፕ ለኮትዲቯር ሪፐብሊክ ጦር ኃይሎች መስከረም 7 ቀን ተላልፏል። እ.አ.አ. 1975 ጀምሮ ስራ ላይ የነበረው ወታደራዊ ካምፕ ከጸጥታ እጦት ጋር ተያይዞ በአካባቢው ነዋሪዎች በሚደርስበት ወቀሳ የውጥረት ምንጭ እንደነበር ተገልጿል። በ2022 በእውነተኛ ጥይት ሲደረግ በነበረ ልምምድ አንድ ነዋሪ እና በርካታ ከብቶች ተገድለዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ተኩስ ታግዶ ቆይቷል። ባለሥልጣናቱ "ለሕዝብ እና ለኮትዲቯር መከላከያ ኃይሎች ጥቅም" ካምፑን በድጋሚ ለመክፈት ከሁሉም አካላት ጋር በጋራ እንደሚሰሩ  የቱሞዲ ዲፓርትመንት ሃላፊ በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተናግረዋል። የፈረንሳይ ጦር ከካምፑ የወጣው የፈረንሳይ ወታደሮች ቡርኪናፋሶ፣ ማሊ እና ኒጀርን ጨምሮ ከበርካታ ሀገራት ለቀው እንዲወጡ እየተገደዱ ባለበት ወቅት ነው።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0