የመስከረም 9 ምሽት አበይት የዓለም ጉዳዮች፦

ሰብስክራይብ
የመስከረም 9 ምሽት አበይት የዓለም ጉዳዮች፦ 🟠 የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሴንት ፒተርስበርግ በሚገኝ ማምረቻ ድሮኖችን የጎበኙ ሲሆን በ2023 የሩሲያ ኃይሎች 140,000 የተለያዩ ዓይነት ድሮኖች እንደደረሷቸውና በ2024 ቁጥሩ በአስር እጥፍ እንደሚጨምር ተናግረዋል። 🟠 የአውሮፓ ፓርላማ ዩክሬን የምዕራባውያን የጦር መሳሪያዎችን በመጠቀም ሩሲያ ውስጥ ዘልቃ እንዳታጠቃ ተቀምጦ የነበረው ገደብ እንዲነሳ ሃሳብ ማቅረቡን ተከትሎ ሊፈርስ ይገባል ሲሉ የሩሲያ ህግ አውጪ ምክር ቤት ሊቀመንበር ቭያቼስላቭ ቮሎዲን ተናገሩ። ሃሳቡ የኒውክሌር ጦር መሳሪያን ወደሚያጠቃልል የዓለም ጦርነት የሚያመራ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። 🟠 ጀርመን 22 ተጨማሪ ሌፐርድ 1A5 ታንኮች እና ሶስት በራሳቸው የሚንቀሳቀሱ ጌፓርድ ፀረ-ጄት መድፎችን ለዩክሬን ማስረከቧን የጀርመን መንግሥት አስታውቋል። 🟠 የሄዝቦላ መሪ ሀሰን ናስራላህ በሊባኖስ የደረሰውን የኤሌክትሮኒክስ ፍንዳታ ከባድ የሽብር ጥቃትና "የዘር ማጥፋት" እንዲሁም የጦርነት እወጃ ነው ሲሉ ገልጸውታል። 🟠 የእስራኤል አውሮፕላኖች በደቡብ ሊባኖስ በሚገኙ በርካታ ቦታዎች ላይ በተመሳሳይ ጊዜ ጥቃት እየፈጸሙ መሆናቸውን የሊባኖስ ምንጮች ዘግበዋል። 🟠 የአሜሪካ የጤና ስርዓት ከአስር የበለፀጉ ሀገራት ዝቅተኛ ደረጃ እንደተሰጠው የአሜሪካ ፋውንዴሽን ኮመንዌልዝ ፈንድ ጥናት አመልክቷል።መረጃዎቹን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0