ሴቶች በአፍሪካ ሰላም፣ ልማት እና ብሩህ ተስፋ እንዲሰፍን ግንባር ቀደም ሆነው መምራት አለባቸው ሲሉ የቀድሞ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ተናገሩ የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ንጦስዛና ድላሚኒ ዙማ "ሴቶች በጋራ ሆነን ያገኘናቸውን ድሎች መጠበቃችንን ማረጋገጥ አለብን፤ ሆኖም የተቀመጡ ገደቦችን አሁንም መግፋታችንን መቀጠል አለብን" ሲሉ ሴንት ፒተርስበርግ ከሚካሄደው 4ኛው የዩሬዢያ የሴቶች መድረክ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ የተናገሩ ሲሆን ሴቶች በህብረተሰቡ ውስጥ ሙሉ እና እኩል ተሳታፊ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ጥረቶች እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል። የሩሲያ እና ደቡብ አፍሪካን የሁለትዮሽ ግንኙነት ያነሱት ዙማ በተለይ የደቡብ አፍሪካ ወጣቶችን ክህሎት በማዳበር፣ በንግድ፣ በቱሪዝም እና በሳይንስ ትብብር ግኑኝነታቸውን የበለጠ ማጠናከር የሚችሉበት እድል እንዳለ እምነታቸውን ገልጸዋል። የቀድሞው የአፍሪካ ህብረት ኃላፊ ሩሲያ የአፍሪካ ሀገራትን የምትደግፍበት መንገድ ከምዕራባውያን ሀገሮች ጋር ያነጻጸሩ ሲሆን ሩሲያ አፍሪካን የትብብር አጋር አድርጋ ስትመለከት ምዕራባውያኑ ግን አብዛኛውን ጊዜ የብዝበዛ አካሄድን ይከተላሉ ብለዋል። "ሩሲያ አፍሪካን አብሮ መስራት የሚቻልበት አህጉር አድርጋ ትመለከታለች። በሚችሉት መንገድ የመርዳት ፍላጎት አላቸው። የምዕራባውያን ሀገራት ከዚህ የተለየ አካሄድ አላቸው" ሲሉ የተናገሩት ዙማ "እንደ ሩሲያ ያሉ ወዳጆች ስላሉን በጣም እናመሰግናለን" ብለዋል። ዲፕሎማቱ የሴቶችን ልዩ ምልከታ እና አስተዋጽኦ ግንዛቤ ውስጥ በመክተት በግጭት መከላከል እና የሰላም ግንባታ የበለጠ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ሴቶች በአፍሪካ ሰላም፣ ልማት እና ብሩህ ተስፋ እንዲሰፍን ግንባር ቀደም ሆነው መምራት አለባቸው ሲሉ የቀድሞ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ተናገሩ
ሴቶች በአፍሪካ ሰላም፣ ልማት እና ብሩህ ተስፋ እንዲሰፍን ግንባር ቀደም ሆነው መምራት አለባቸው ሲሉ የቀድሞ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ተናገሩ
Sputnik አፍሪካ
ሴቶች በአፍሪካ ሰላም፣ ልማት እና ብሩህ ተስፋ እንዲሰፍን ግንባር ቀደም ሆነው መምራት አለባቸው ሲሉ የቀድሞ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ተናገሩ የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ንጦስዛና ድላሚኒ ዙማ... 19.09.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-09-19T09:43+0300
2024-09-19T09:43+0300
2024-09-19T10:04+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ሴቶች በአፍሪካ ሰላም፣ ልማት እና ብሩህ ተስፋ እንዲሰፍን ግንባር ቀደም ሆነው መምራት አለባቸው ሲሉ የቀድሞ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ተናገሩ
09:43 19.09.2024 (የተሻሻለ: 10:04 19.09.2024)
ሰብስክራይብ