የመስከረም 8 ምሽት አበይት የዓለም ጉዳዮች፦

ሰብስክራይብ
የመስከረም 8 ምሽት አበይት የዓለም ጉዳዮች፦ 🟠 በሊባኖስ በደረሰ ተጨማሪ የመገናኛ መሳሪያዎች ፍንዳታ አንድ ሰው ሲሞት ከ100 በላይ መቁሰላቸውን የሊባኖስ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ ክፍል ማእከል ገለጸ። 🟠 የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከብራዚል ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ ጋር ባደረጉት ውይይት ከሰደድ እሳት ለማጋገም የሚደረጉ ጥረቶችን ለመደገፍ ፍላጎት እንዳላቸው አስታወቁ። 🟠 በሩሲያ ትቬር ክልል በወደቀ የድሮን ስብርባሪ 13 ሰዎች መካከለኛ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል እንደገቡ የሩሲያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገለጸ። 🟠 ፊንላንድ ሁለት የኔቶ ዋና መሥሪያ ቤቶችን አንደኛውን በሰሜን ሌላኛውን በደቡብ ሩሲያ ድንበር አቅራቢያ እንደምትከፍት የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ።🟠 የሩሲያ እና የቻይና የባህር ዳርቻ ጥበቃ አገልግሎቶች ለመጀመሪያ ጊዜ በሩሲያ ቭላዲቮስቶክ የጋራ ልምምድ አደረጉ።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0