አዲስ አበባ በፈረንጆቹ 2035 የአፍሪካ ቁልፍ ከተማ ትሆናለች ተባለ

ሰብስክራይብ
አዲስ አበባ በፈረንጆቹ 2035 የአፍሪካ ቁልፍ ከተማ ትሆናለች ተባለ ኢኮኖሚኪ ኢንተለጀንስ "የአፍሪካ ከተሞች 2035" በሚል ርዕስ ባወጣው ሪፖርት አዲስ አበባ እያስመዘገበች ላለው ለውጥ እውቅና ሰጥቷል። የአዲስ አበባ ኢኮኖሚ ከአፍሪካ ከፍተኛ ፍጥነት ያለውን ዕድገት እንደሚያሳይ የገለጸው ሪፖርቱ መዲናዋ እስከ ፈረንጆቹ 2035 ድረስ በዓመት ባለ ሁለት አሃዝ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት (ጂዲፒ) እንደምታስመዘግብ አስታውቋል።የኮንጎ ሪፐብሊኳ ብራዛቪል፣ የታንዛኒያዋ ዳሬሰላም እና የአንጎላ መዲና ሉዋንዳ በመጪው አስር ዓመት አዲስ አበባን ተከትለው የሚያድጉ የአህጉሪቱ ከተሞች እንደሆኑ ሪፖርቱ አመልክቷል። የአፍሪካ ትልልቅ ከተሞች ካይሮ፣ ሌጎስ እና ጆሀንስበርግ በኢኮኖሚ የበላይነታቸው እንደሚቀጥሉም ሪፖርቱ ጠቁሟል።ምስሉ ከማህበራዊ ትስስር ገጾች የተገኘ ነው መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0