ዚምባብዌ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣው የዓለም የወርቅ ፍላጎት መጠቀም እንደምትፈልግ አስታወቀች የዚምባብዌ ማዕድንና ማዕድን ልማት ሚኒስቴር የወርቅ ምርትና ገቢን ለማሳደግ “2024 ሁለተኛ የወርቅ ንቅናቄ” የተሰኘ ሀገር አቀፍ ተነሳሽነት አስጀምሯል። ግቡ በማስፋፊያ እና የዋጋ ጭማሬ በ2023 የነበረውን 33 ቶን ምርት በ2024 ወደ 39 ቶን ማሳደግ ነው። ይህም በዚህ ዓመት ከ3 ቢልየን ዶላር በላይ ገቢ ለማመንጨት ይረዳል። ተነሳሽነቱ በ2024 የዘርፉን አቅም በ95% ለመጠቀም በሁሉም የማዕድን ስራዎች ላይ የህግ ተገዢነት እና ውጤታማነትን ማሳደግ ትኩረቱ ያደርጋል። ፕሮግራሙ ስምንት ክልሎችን የሚሸፍን ሲሆን የወርቅ ምርትን ለማሳደግ እና ከከፍተኛ ዓለም አቀፍ ፍላጎት ለመጠቀም ከትልቅ እስከ አነስተኛ ማዕድን ማውጫዎች ጋር በመተባበር ይሰራል። ዚምባብዌ ህገ-ወጥ የወርቅ ንግድን ለመዋጋት ሁሉንም የወርቅ ወጪ ንግድ ፊደልቲ ጎልድ በተሰኘ በመንግስት ባለቤትነት በተያዘ እና በሀገር ውስጥ ማዕድን አውጪዎች የሚመረተውን ወርቅ ለመግዛት፣ ለማጣራት እና ለመሸጥ ሃላፊነት በተሰጠው ተቋም በኩል እንዲያልፍ በማድረግ ገቢ ለማሳደግ እና መገበያያዋን ለመደገፍ ትፈልጋለች።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ዚምባብዌ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣው የዓለም የወርቅ ፍላጎት መጠቀም እንደምትፈልግ አስታወቀች
ዚምባብዌ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣው የዓለም የወርቅ ፍላጎት መጠቀም እንደምትፈልግ አስታወቀች
Sputnik አፍሪካ
ዚምባብዌ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣው የዓለም የወርቅ ፍላጎት መጠቀም እንደምትፈልግ አስታወቀች የዚምባብዌ ማዕድንና ማዕድን ልማት ሚኒስቴር የወርቅ ምርትና ገቢን ለማሳደግ “2024 ሁለተኛ የወርቅ ንቅናቄ” የተሰኘ ሀገር አቀፍ ተነሳሽነት... 18.09.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-09-18T10:08+0300
2024-09-18T10:08+0300
2024-09-18T10:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ዚምባብዌ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣው የዓለም የወርቅ ፍላጎት መጠቀም እንደምትፈልግ አስታወቀች
10:08 18.09.2024 (የተሻሻለ: 10:44 18.09.2024)
ሰብስክራይብ