ብሪክስ በዓለም አቀፍ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ ሚዛን አለው ስትል ባኩ ተናገረች

ሰብስክራይብ
ብሪክስ በዓለም አቀፍ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ ሚዛን አለው ስትል ባኩ ተናገረች ድርጅቱ በዓለም ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ውስጥ ከሚጫወተው ትልቅ ሚና አኳያ አዘርባጃን ብሪክስን መቀላቀል እንደምትሻ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሬስ አገልግሎት ኃላፊ አይሀን ሃጂዛዴህ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። ቃል አቀባዩ ሀገሪቱ ባሳለፍነው ዓመት መጋቢት 24 ቀን ለብሪክስ አባልነት ይፋዊ ማመልከቻ ማቅረቧን አስታውቀዋል። ሌሎች ከ30 በላይ ሀገራት የአባልነት ጥያቄ ማቅረባቸው እና በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ሀገራት መኖራቸው ለድርጅቱ ያለው ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱን ያሳያል። የሚኒስቴሩ ተወካይ አክለውም ድርጅቱ ከፍተኛ አቅም ያለው በመሆኑ ማራኪ ነው ብለዋል። ብሪክስ ከ30% በላይ የሚሆነውን የዓለም ክፍል፣ 43% ህዝብ እና ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ውስጥ 26% ይሸፍናል። የድርጅቱ አባል ሀገራት ከፍተኛ የተፈጥሮ ሃብት፣ ትልቅ የሀገር ውስጥ ገበያ እና የሰው ሃይል እንዲሁም አንዳንድ አባላት ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪዎች እንዳላቸውም ኃላፊው ጠቁመዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0