ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ወደ ውጭ የሚላከውን የነዳጅ ምርት እንደገና ለመጀመር እርምጃ ሊወስዱ መሆኑን የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ገለፁ

ሰብስክራይብ
ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ወደ ውጭ የሚላከውን የነዳጅ ምርት እንደገና ለመጀመር እርምጃ ሊወስዱ መሆኑን የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ገለፁየነዳጅ ዘይት ወደ ውጭ መላክ ለደቡብ ሱዳን ወሳኝ የገቢ ምንጭ ሲሆን ሱዳን የመሸጋገሪያ ክፍያ ትሰበስባለች። የደቡብ ሱዳንን የነዳጅ ዘይትን በሱዳን በኩል ለውጭ ገበያ የሚያስተላልፈው መስመር ከየካቲት ወር ጀምሮ በሱዳን ጦር ኃይል እና በፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች መካከል በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ ችግር ገጥሞታል። "የደቡብ ሱዳን መሐንዲሶች በቀጣይ ሳምንታት ወደ ሱዳን በመሄድ ምርቱን ለማስተላለፍ የመስመሮቹን ዝግጁነት ለመገምገም እንደሚሄዱ ይጠበቃል" ሲሉ የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ረመዳን ጎክ ተናግረዋል።ደቡብ ሱዳን እ.ኤ.አ በ2011 ከካርቱም ነፃ ከወጣች በኋላ በቀን 150,000 በርሜል ድፍድፍ ዘይት በሱዳን በኩል ልካለች፤ በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት የምርቱ መጠን በቀን 350,000-400,000 በርሜል ደርሷል።የደቡብ ሱዳን ኢኮኖሚ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተለያዩ ምክንያቶች ተዳክሟል ፤ የህብረተሰብ ግጭት፣ ከ2013-2018 የተካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት እና በጎረቤት ሱዳን ጦርነት ሳቢያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የወጪ ንግድ መስተጓጎል ገጥሞታል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0