ኢትዮጵያ እና ቻይና ወታደራዊ ትብብራቸውን ለማሳደግ ተስማሙየኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሚመራው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ወታደራዊ ልዑክ በ11ኛው የቤጂንግ ዢያንግሻን ፎረም ላይ እየተሳተፈ ነው።11ኛው የቤጂንግ ዢያንግሻን ፎረም ከ100 በላይ ሀገራትና ድርጅቶች እየተሳተፉ ሲሆን "ሰላም ለጋራ ተጠቃሚነት" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ነው።በዝግጅቱ በአለም አቀፍ ደህንነት፣ በቀጣናዊ መረጋጋት እና በመከላከያ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ላይ ወሳኝ ውይይቶችን ተካሂዷል።ከመድረኩ ጎን ለጎን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ከቻይና ማዕከላዊ ወታደራዊ ኮሚሽን አባል እና ከቻይና ማዕከላዊ ወታደራዊ ኮሚሽን የጋራ ስታፍ ዲፓርትመንት ዋና ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሊዩ ዠንሊ ጋር ተወያይተዋል።በውይይቱ ወቅት ሁለቱም ወገኖች በአምስተኛው-ትውልድ ጦርነት (5GW)፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በወታደራዊ መሳሪያዎች እና በወታደራዊ አቅም ግንባታ ዘርፎች በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን ፤ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ እና ዠንሊ የመግባቢያ ሰነድ (MoU) ተፈራርመዋል።ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችም የሁለትዮሽ ወታደራዊ ትብብርን ወደ አዲስ ከፍታ ከፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን መከላከያ የማህበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ አስፍሯል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ኢትዮጵያ እና ቻይና ወታደራዊ ትብብራቸውን ለማሳደግ ተስማሙ
ኢትዮጵያ እና ቻይና ወታደራዊ ትብብራቸውን ለማሳደግ ተስማሙ
Sputnik አፍሪካ
ኢትዮጵያ እና ቻይና ወታደራዊ ትብብራቸውን ለማሳደግ ተስማሙየኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሚመራው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ወታደራዊ ልዑክ በ11ኛው የቤጂንግ ዢያንግሻን ፎረም ላይ እየተሳተፈ ነው።11ኛው... 16.09.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-09-16T20:11+0300
2024-09-16T20:11+0300
2024-09-16T20:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий