ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካ የነፃነት እና የአንድነት ምልክት ናት ሲሉ የሴራሊዮን የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩየሴራሊዮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ፕሮፌሰር ዴቪድ ፍራንሲስ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካን እሴት የሆኑትን ነጻነት፣ አንድነት እና ተጋድሎ እሴቶችን በማስተዋወቅ ረገድ የተጫወተችው ታሪካዊ ሚና ወደር የለውም። ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መገኛ እና ቅኝ አገዛዝን የተቃወመች ብቸኛዋ አፍሪካዊት ሀገር እንደመሆኗ መጠን ለአህጉሪቱ የተስፋ እና የስልጣኔ ምልክት ሆና ቆይታለች። "ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መገኛ ናት። ታዲያ ያ ምን ማለት ነው? በሁለት ምክንያቶች ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካኒዝም ማዕከል ሆናለች ማለት ነው። በመጀመሪያ ስለ አድዋ ድል ልናገር። አድዋ የተቀሩት አፍሪካ ሀገራትም ድል ነው። አድዋ የአፍሪካ የነፃነት ምልክት ነው። በልዩነት ውስጥ አንድነትን ማምጣት እንችላለን። [...] ከሁሉም በላይ የጥቁር ህዝቦች ኩራት፣ የቅርስ፣ የነፃነት እና በአለም አቀፍ ደረጃ የ እምቢ ባይነት ምልክት ነው ሲሉ የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለኢዜአ ተናግረዋል።ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታ ጀምሮ የአፍሪካ ህብረት ዋና መሥሪያ ቤት መቀመጫ እስከመሆን ድረስ፣ ኢትዮጵያ ለፓን አፍሪካን ፅንሰ-ሀሳቦች ያላት ቁርጠኝነት ለአፍሪካ ነፃነትና አብሮነት በሚደረገው ትግል የማያቋርጥ ኃይል ሆኖ ቆይቷል ሲሉም አክለዋል።እ.አ.አ መጋቢት 1 ቀን 1896 በዳግማዊ አፄ ምኒልክ የሚመራው የኢትዮጵያ ኢምፓየር ጦር የኢጣሊያንን ወራሪ ጦር በአድዋ ጦርነት በማሸነፍ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያስከበረበት እና የፓን አፍሪካኒዝም ዋነኛ ምልክት የሆነበትን ወሳኝ ድል የረጋገጠበት ዓመት ነበር።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች Google play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካ የነፃነት እና የአንድነት ምልክት ናት ሲሉ የሴራሊዮን የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ
ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካ የነፃነት እና የአንድነት ምልክት ናት ሲሉ የሴራሊዮን የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ
Sputnik አፍሪካ
ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካ የነፃነት እና የአንድነት ምልክት ናት ሲሉ የሴራሊዮን የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩየሴራሊዮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ፕሮፌሰር ዴቪድ ፍራንሲስ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካን እሴት የሆኑትን ነጻነት፣... 16.09.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-09-16T13:32+0300
2024-09-16T13:32+0300
2024-09-16T14:04+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካ የነፃነት እና የአንድነት ምልክት ናት ሲሉ የሴራሊዮን የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ
13:32 16.09.2024 (የተሻሻለ: 14:04 16.09.2024)
ሰብስክራይብ