ሶማሊያ በኢትዮጵያ ለሚገኙ አማፂያን የጦር መሳሪያ ለማቅረብ መዘጋጀቷን አስታወቀችአዲስ አበባ የባህር በር ለማግኘት ከሶማሊያ ተገንጥላ ራስ ገዝ ከሆነችው ሶማሌላንድ ጋር ባሳለፍነው ዓመት ታህሳስ ወር ያደረገችውን ስምምነት ተግባራዊ የምታደርግ ከሆነ ሶማሊያ በኢትዮጵያ ለሚገኙ አማፂያን የጦር መሳሪያ ታቀርባላች ሲሉ የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ ሞአሊም ፊቂ ተናግረዋል። "በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታገሉትን አማፂያን የመደገፍ ወይም የኢትዮጵያን አገዛዝ የመጋፈጥ ምርጫው ክፍት ነው" ማለታቸውን ዩኒቨርሳል ሶማሌ ቲቪ ሚኒስትሩን ጠቅሶ ዘግቧል። "ኢትዮጵያ ጠላትነቷን ከቀጠለች እና ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገችውን ስምምነት ተግባራዊ ካደረገች ከአማፂያኑ ጋር መተባበር እና መደገፍ ትክክል ይሆናል።"በዚህ ሳምንት የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሳ ካይድ "የሶማሌላንድ እና ኢትዮጵያ የመግባቢያ ስምምነት እንደተገናቀቀ እና ወደ መደበኛ የህግ ስምምነት መቀየሩ የማይቀር ነው" ማለታቸው ይታወሳል።በነሀሴ ወር መጀመሪያ ላይ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አፅቀ ስላሴ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል እየተደረገ ያለው ድርድር መሻሻሎች እንዳሉት እውቅና ሰጥተዋል። ሆኖም ቀስቃሽ ንግግሮች እና ድርጊቶች ግስጋሴውን እንዳያበላሹ መፍቀድን የለብንም ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ከጠላት ሃይሎች ጋር የሚደረገው ጥምረት አርቆ አስተዋይነት የጎደለው እና የሀገራቱን ግንኙነት የሚጎዳ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ሶማሊያ በኢትዮጵያ ለሚገኙ አማፂያን የጦር መሳሪያ ለማቅረብ መዘጋጀቷን አስታወቀች
ሶማሊያ በኢትዮጵያ ለሚገኙ አማፂያን የጦር መሳሪያ ለማቅረብ መዘጋጀቷን አስታወቀች
Sputnik አፍሪካ
ሶማሊያ በኢትዮጵያ ለሚገኙ አማፂያን የጦር መሳሪያ ለማቅረብ መዘጋጀቷን አስታወቀችአዲስ አበባ የባህር በር ለማግኘት ከሶማሌ ተገንጥላ ራስ ገዝ ከሆነችው ሶማሌ ላንድ ጋር በያዝነው አመት ጥር ወር የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ የምታደርግ ከሆነ ሶማሊያ... 15.09.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-09-15T16:14+0300
2024-09-15T16:14+0300
2024-09-15T20:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ሶማሊያ በኢትዮጵያ ለሚገኙ አማፂያን የጦር መሳሪያ ለማቅረብ መዘጋጀቷን አስታወቀች
16:14 15.09.2024 (የተሻሻለ: 20:44 15.09.2024)
ሰብስክራይብ