አፍሪካ ሲዲሲ ለኤምፖክስ ምላሽ 600 ሚሊዮን ዶላር ማሰባሰብ እንደሚችል ገለጸ

ሰብስክራይብ
አፍሪካ ሲዲሲ ለኤምፖክስ ምላሽ 600 ሚሊዮን ዶላር ማሰባሰብ እንደሚችል ገለጸ "600 ሚሊየን ዶላሩን መሰብሰብ እንደምንችል እርግጠኛ እንደሆንኩ ማወቅ ከፈለጋችሁ፤ በእርግጠኝነት አዎ ማለት እችላለሁ" ሲሉ የአፍሪካ ሲዲሲ ዋና ዳይሬክተር ዣን ካሴያ መናገራቸውን ተዘግቧል። ገንዘቡ ከአፍሪካ ህብረት ሀገራት፣ ከልማት አጋሮች፣ ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ከግሉ ሴክተር መዋጮ ይሰበሰባል። እንደ ጋቪ እና ዘ ፓንዴሚክ ፈንድ ካሉ ድርጅቶች ጋር ውይይት እየተካሄደ ሲሆን የቴክኖሎጂ ዝውውሮች የክትባት ወጪዎችን 90% ሊቀንስ እንደሚችል ተገልጿል። በተጨማሪም የምዕራቡ ዓለም ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ትምህርት መውሰዱን እና በኤምፖክስ ወረርሽኝ ወቅት አፍሪካን እንዳልተወ ማሳየት እንደሚጠበቅበት ኃላፊው አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። "እንደምናውቀው በምዕራብ ሀገራት እና በአፍሪካ መካከል ያለው መተማመን ተሰብሯል። አሁን ጊዜው የአብሮነት ነው" ብለዋል ካሴያ። ይህ ጥረት የዓለም ጤና ድርጅት ኤምፖክስን በነሐሴ ወር ዓለም አቀፍ ድንገተኛ የጤና አደጋ ነው ብሎ ካወጀ በኋላ የመጣ ነው። በዲሞክራሲያዊ ኮንጎ ሪፐብሊክ የተከሰተው ወረርሽኝ ወደ ጎረቤት ሀገራት የተዛመተ ሲሆን በ2024 ብቻ ከ26,000 በላይ በበሽታው ተይዘዋል ተብሎ የተጠረጠሩ እና 724 የሞቱ ሰዎች ተመዝግበዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0