ሲሸልስ ወደ ሩሲያ የቀጥታ በረራዎችን የምታስፋበትን መንገድ እየፈለገች እንደሆነ ተገለጸ

ሰብስክራይብ
ሲሸልስ ወደ ሩሲያ የቀጥታ በረራዎችን የምታስፋበትን መንገድ እየፈለገች እንደሆነ ተገለጸ የሲሼልስ የወጣቶች፣ ስፖርት እና ቤተሰብ ጉዳዮች ሚኒስትር ሜሪ-ሴሊን ዚያሎር "ወደ ሩሲያ የሚደረጉ የቀጥታ በረራዎችን በማሻሻል እና በማሳደግ ተጨማሪ የሩሲያ ቱሪስቶችን ለመሳብ እና የተሻለ የህዝብ ለህዝብ ግኑኝነት ለመፍጠር መታቀዱን" ለስፑትኒክ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ አክለውም አሁን ያለው የፖለቲካ ሁኔታ እንዳለ ሆኖ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት አዎንታዊ ሆኖ ከ40 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ረጅም ታሪክ እንዳለው አመልክተዋል። የባህልና ስፖርት ልውውጦች ፖለቲካዊ ልዩነቶችን ያስወግዳሉ ብለው እንደሚያምኑ የገለጹት ዚያሎር ይህንን መልእክት ለወጣቱ ትውልድ ማድረስ አስፈላጊ ነው ብለዋል። "ባህልና ስፖርት ከፖለቲካ በላይ ናቸው። ወሳኙ ነገር ይህ ነው፤ ይህንን መልእክት ነው ለወጣቶቻችን ልናስተላልፈው የሚገባው" ብለዋል ሚኒስትሩ። ሚኒስትሯ አክለውም ከሩሲያ የባህል ሚኒስትር ኦልጋ ሊዩቢሞቫ ጋር በወጣቶች፣ ኪነ-ጥበብ እና ባህል መስኮች ሊኖሩ ስለሚችሉ የትብብር መንገዶች አርብ እለት እንደሚወያዩ ተናግረዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0