ሶማሌላንድ እና ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ወደብ በርበራ አጠቃቀም ዙርያ የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት እየተጠናቀቀ እንደሆነ ተገለጸ "የሶማሌላንድ-ኢትዮጵያ የመግባቢያ ስምምነት ተጠናቋል፤ ኦፊሴላዊ የህግ ስምምነት በቅርቡ ይደረጋል" ሲሉ የተገንጣይዋ ሶማሊላንድ ግዛት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሳ ካይድ በሃርጌሳ ከውጪ አምባሳደሮች ጋር ባደረጉት ውይይት ተናግረዋል። የሶማሊላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ የቴክኒክ ቡድን፣ የዓለም አቀፍ የህግ ባለሙያዎች ቡድን እና ከፍተኛ አማካሪ ቡድን እንደቀጠረ ቀደም ሲል አስታውቋል። የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በበኩላቸው ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት ወደብ የማግኘት ተጨማሪ እድሎችን ለመፍጠር ለጋራ ስምምነት መርሆዎች ትኩረት በመስጠት የመግባቢያ ሰነዱን "ተግባራዊ" ለማድረግ እንዳሰቡ መግለጻቸውን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ታህሳስ 22 ቀን 2016 የተፈረመው የሶማሌላንድ እና ኢትዮጵያ የመግባቢያ ስምምነት ሉዓላዊነቴን የጣሰ ነው በምትለው ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን “ውጥረት ለማርገብ” ጂቡቲ በኤደን ባሕረ ሰላጤ የሚገኘውን የታጁራ ወደብ በጋራ የማስተዳደር ሃሳብ ለአዲስ አበባ ማቅረቧ የሚታወስ ነው።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ሶማሌላንድ እና ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ወደብ በርበራ አጠቃቀም ዙርያ የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት እየተጠናቀቀ እንደሆነ ተገለጸ
ሶማሌላንድ እና ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ወደብ በርበራ አጠቃቀም ዙርያ የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት እየተጠናቀቀ እንደሆነ ተገለጸ
Sputnik አፍሪካ
ሶማሌላንድ እና ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ወደብ በርበራ አጠቃቀም ዙርያ የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት እየተጠናቀቀ እንደሆነ ተገለጸ "የሶማሌላንድ-ኢትዮጵያ የመግባቢያ ስምምነት ተጠናቋል፤ ኦፊሴላዊ የህግ ስምምነት በቅርቡ ይደረጋል" ሲሉ የተገንጣይዋ... 13.09.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-09-13T10:02+0300
2024-09-13T10:02+0300
2024-09-13T10:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ሶማሌላንድ እና ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ወደብ በርበራ አጠቃቀም ዙርያ የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት እየተጠናቀቀ እንደሆነ ተገለጸ
10:02 13.09.2024 (የተሻሻለ: 10:44 13.09.2024)
ሰብስክራይብ