የብሪክስ ትብብር ባለ ብዙ ወገን ግኑኝነት እና የተባበሩት መንግሥታትን ተሃድሶ ያጠናክራል ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣን ተናገሩ በሴንት ፒተርስበርግ እየተካሄደ ባለው የብሪክስ ከፍተኛ የጸጥታ ሃላፊዎች ስብሰባ ላይ ከስፑትኒክ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና አማካሪ ዓብዱልዓዚዝ አህመድ አደም ዓለም አቀፍ የጸጥታ ችግሮችን ለመቅረፍ ትብብር አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል። "የዓለማችንን ተግዳሮቶች ለመጋፈጥ በሀገራዊ፣ ክልላዊ እና ንዑስ ክልላዊ ደረጃ በጸጥታ፣ በመረጃ ልውውጥ ትብብር በመፍጠር ከአንድ ወገን እርምጃዎች ይልቅ የባለብዙ ወገን ስርዓትን እውን ለማድረግ በጋራ አየሰራን ነው" ብለዋል። የዓለም የጸጥታ ሁኔታ “በተግዳሮቶች የተሞላ” ነው ያሉት ዋና አማካሪው በርካታ ግጭቶችን እና የአንድ ወገን እርምጃዎችን የሚያራምዱ ኃያላን ሀገራትን እየጨመረ የመጣ ተጽእኖ ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ ብሪክስን ከተቀላቀለች አንደኛ ዓመቷ ላይ ብትሆንም በተለያዩ ጊዜያት በብሪክስ የጸጥታ ፎርማት በመሳተፍ ከቡድኑ ጋር በፈጠረችው ትብብር የዓለም አቀፍ የጸጥታ ስጋቶችን ለመቅረፍ ቁርጠኛ እንደሆነች አሳይታለች ብለዋል። "ብሪክስ የባለ ብዙ ወገን ስርዓትን ለማጠናከር እና የተባበሩት መንግሥታትን ለመለወጥ የሚደረገውን ሂደት ያግዛል። ይህ ዓለምን እንዲሁም የብሪክስ ሀገራትን የሚጠቅም ይሆናል" ሲሉ ተናግረዋል። በብሪክስ ፎርማት ለኢትዮጵያ በጣም አስፈላጊው አጀንዳ በመንግሥታት ስፖንሰር የሚደረገውን ጨምሮ ሁሉንም ዓይነት ሽብርተኝነት መዋጋት መሆኑን አማካሪው ጨምረው ገልጸዋል። ይህንን ውስብስብ እና እየተስፋፋ የመጣ ስጋት ለመፍታት ትብብር እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የብሪክስ ትብብር ባለ ብዙ ወገን ግኑኝነት እና የተባበሩት መንግሥታትን ተሃድሶ ያጠናክራል ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣን ተናገሩ
የብሪክስ ትብብር ባለ ብዙ ወገን ግኑኝነት እና የተባበሩት መንግሥታትን ተሃድሶ ያጠናክራል ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣን ተናገሩ
Sputnik አፍሪካ
የብሪክስ ትብብር ባለ ብዙ ወገን ግኑኝነት እና የተባበሩት መንግሥታትን ተሃድሶ ያጠናክራል ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣን ተናገሩ በሴንት ፒተርስበርግ እየተካሄደ ባለው የብሪክስ ከፍተኛ የጸጥታ ሃላፊዎች ስብሰባ ላይ ከስፑትኒክ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት... 12.09.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-09-12T15:59+0300
2024-09-12T15:59+0300
2024-09-12T16:04+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የብሪክስ ትብብር ባለ ብዙ ወገን ግኑኝነት እና የተባበሩት መንግሥታትን ተሃድሶ ያጠናክራል ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣን ተናገሩ
15:59 12.09.2024 (የተሻሻለ: 16:04 12.09.2024)
ሰብስክራይብ