ኢትዮጵያዊቷ ታዳጊ ኮከብ በቪዛ ጉዳይ ከዳይመንድ ሊግ ፍፃሜ ውጪ ሆነች የ2024 ከ20 ዓመት በታች የ3000 ሜትር መሰናክል የዓለም ሻምፒዮን እና የኢትዮጵያ አትለቲክስ ታዳጊ ኮከብ ሰምቦ አለማየሁ በሚቀጥለው ሳምንት በብራሰልስ በሚደረገው የዳይመንድ ሊግ ፍፃሜ በቪዛ ምክንያት እንደማትሳተፍ ከ100 በላይ የኢትዮጵያ እና ኬንያ አትሌቶችን የሚወክለው ኢሊት የሯጮች ቡድን አስታወቀ። የዳይመንድ ሊግ ውድድር አሸናፊዋ፣ በቅርቡ በተካሄደው የፓሪስ ኦሊምፒክ አምስተኛ ሆና ያጠናቀቀችው እና ከ20 ዓመት በታች የ3000 ሜትር መሰናክል የኢትዮጵያን ክብረ ወሰን የያዘችው ሰምቦ የሸንገን ዞን ቪዛ በጊዜ ማግኘት ባለመቻሏ ከውድድሩ ውጪ ሆናለች። በሚያዚያ ወር 2024 የአውሮፓ ህብረት ይፋ ያደረገው እርምጃ የኢትዮጵያን ዜጎች ቪዛ የማግኘት እድል ማክበዱ ለጉዳዩ አስተዋፅኦ እንዳለው የአትሌቷ ተወካይ ጠቁሟል። "ይህ ሁኔታ የበርካታ አትሌቶች እድሎችን እና ህይወት እየጎዳ ነው። በተቻለ ፍጥነት እንደሚፈታ አጥብቀን ተስፋ እናደርጋለን" ብሏል ቡድኑ በጋዜጣዊ መግለጫው። ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ኢትዮጵያዊቷ ታዳጊ ኮከብ በቪዛ ጉዳይ ከዳይመንድ ሊግ ፍፃሜ ውጪ ሆነች
ኢትዮጵያዊቷ ታዳጊ ኮከብ በቪዛ ጉዳይ ከዳይመንድ ሊግ ፍፃሜ ውጪ ሆነች
Sputnik አፍሪካ
ኢትዮጵያዊቷ ታዳጊ ኮከብ በቪዛ ጉዳይ ከዳይመንድ ሊግ ፍፃሜ ውጪ ሆነች የ2024 ከ20 ዓመት በታች የ3000 ሜትር መሰናክል የዓለም ሻምፒዮን እና የኢትዮጵያ አትለቲክስ ታዳጊ ኮከብ ሰምቦ አለማየሁ በሚቀጥለው ሳምንት በብራሰልስ በሚደረገው የዳይመንድ... 12.09.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-09-12T10:49+0300
2024-09-12T10:49+0300
2024-09-12T13:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий