የመስከረም 1 ምሽት አበይት የዓለም ጉዳዮች፦ 🟠 የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዩራኒየም፣ ቲታኒየም፣ ኒኬል እና "አንዳንድ" እቃዎች ላይ የኤክስፖርት ገደብ እንዲጣል ሀሳብ አቀረቡ። 🟠 የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ዩክሬን በሩሲያ ግዛቶች ላይ ከምትፈጽማቸው ጥቃቶች ጀርባ የአሜሪካ፣ ብሪታንያ እና ኔቶ እጅ አለበት ሲሉ ከሰሱ። 🟠 የኪዬቭ አገዛዝ በጥቁር ባህር የሚገኘውን የሩሲያ የነዳጅ ቁፋሮ መዋቅር "Crimea-2" ለመያዝ ያደረገው ሙከራ መክሸፉን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። 🟠 የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴቪድ ላሚ ለዩክሬን ከ600 ሚሊየን ፓውንድ በላይ የገንዘብ ድጋፍ ይፋ አደረጉ። 🟠 ዩክሬን የአሜሪካን የጦር መሳሪያ ተጠቅማ በሩሲያ ግዛት ውስጥ ዘልቃ ጥቃት እንድታካሄድ ይሁንታ መስጠትን በተመለከተ በባይደን አስተዳደር ውስጥ ክፍፍል እንዳለ ሚዲያዎች ዘግበዋል። 🟠 የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ዶናልድ ትራምፕ ከሃሪስ ጋር አዲስ የቴሌቭዥን ክርክር ለማድረግ ፍላጎት እንደሌላቸውና የመጀመሪያው ዙር ለሳቸው ጥሩ እንደነበር ተናግረዋል። 🟠 የስፔስኤክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤለን መስክ ካማላ ሃሪስ የሚያሸንፉ ከሆነ አሜሪካውያን ማርስ አይደርሱም አለ። 🟠 በአውስትራሊያ ሜልቦር ከተማ የተካሄደው ዓለም አቀፍ የጦር መሳሪያ አውደ ርዕይ ላይ የተነሳው ተቃውሞ ተባብሶ ከፍተኛ እረብሻ ተፈጠረ። 🟠 በምዕራብ ህንድ 15 ሰዎች ባልታወቀ በሽታ መሞታቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የመስከረም 1 ምሽት አበይት የዓለም ጉዳዮች፦
የመስከረም 1 ምሽት አበይት የዓለም ጉዳዮች፦
Sputnik አፍሪካ
የመስከረም 1 ምሽት አበይት የዓለም ጉዳዮች፦ 🟠 የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዩራኒየም፣ ቲታኒየም፣ ኒኬል እና "አንዳንድ" እቃዎች ላይ የኤክስፖርት ገደብ እንዲጣል ሀሳብ አቀረቡ። 🟠 የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ዩክሬን... 11.09.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-09-11T20:33+0300
2024-09-11T20:33+0300
2024-09-11T21:04+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий