በኬንያ ናይሮቢ አውሮፕላን ማረፊያ የሚካሄደው አድማ ቀጥሏል

ሰብስክራይብ
በኬንያ ናይሮቢ አውሮፕላን ማረፊያ የሚካሄደው አድማ ቀጥሏል የኬንያ አቪዬሽን ሰራተኞች አየር ማረፊያውን ለህንዱ አዳኒ ግሩፕ ሆልዲንግስ ለማከራየት የተደረገው ስምምነት ከስራ ያፈናቅለናል በማለት ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ። አዳኒ ባቀረበው እቅድ አዲስ ማኮብኮቢያ እንደሚገነባ እና የመንገደኞች ተርሚናሉን እንደሚያድስ ገልጿል። የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረበውን የ30 ዓመት የኪራይ ውል ለጊዜው ቢያግድም የአቪዬሽን ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል። ሰራተኞቹ ኬንያ የምስራቅ አፍሪካ አቪዬሽን ማዕከል እንደመሆኗ ያለ ኪራይ ውሉ አስፈላጊውን ገንዘብ ማግኘት ይቻላል የሚል መከራከሪያ አቅርበዋል። አድማው ወደ ኪሱሙ እና ሞምባሳ የክልል አየር ማረፊያዎች እንደተዛመተ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ምስሎቹ ከማህበራዊ ትስስር ገጾች የተገኙ ናቸውስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0