የጳጉሜ 5 ምሽት አበይት የዓለም ዜናዎች፦

ሰብስክራይብ
የጳጉሜ 5 ምሽት አበይት የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 በ"ኦሺን-2024" ልምምድ በጣም ውስብስብ እና እውነተኛ ውጊያ መሰል ልምምዶች እንደሚካሄዱ ፑቲን ገለጹ። 🟠 ቭላድሚር ፑቲን የቬትናም ፓርላማ አፈ-ጉባዔ ትራን ታንህ ማን በክሬምሊን ተቀበሉ። 🟠 ጀርመን የጀመረችው የድንበር ቁጥጥር ተቀባይነት እንደሌለው እና አስቸኳይ ምክክር እንደሚያስፈልግ የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ተስክ ተናገሩ። በርሊን የስደተኞችን ፍልሰት ለመቀነስ እና ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የድንበር ቁጥጥር መጀመሯን አስታውቃለች። 🟠 የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የዩክሬን ጦር ሩሲያን በረጅም ርቀት መሳሪያ እንዲመታ ፍቃድ በመስጠት ዙርያ ከብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር ጋር በመጪው አርብ እንደሚወያዩ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን አስታወቁ። 🟠 ዋሽንግተን ኢራን ከሩሲያ ጋር በምታደረገው ትብብር ምክንያት ቴህራን ላይ ማክሰኞ አዲስ ማዕቀብ እንደምትጥል እና ማዕቀቡ የኢራንን አየር መንገድ ኢራን ኤይርንም ጭምር እንደሚመለከት ብሊንከን ተናገሩ። 🟠 ከ15% ያላነሰ የደመወዝ ጭማሪ የጠየቁ የማዕድን እና የኢነርጂ ሰራተኞች የፖላንድ መዲና ዋርሶ ማዕከላዊ ክፍልን ዘጉ። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0