የጳጉሜ 5 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 በሞስኮ ክልል ራመንስኮዬ ከተማ በደረሰ የድሮንን ጥቃት የ46 ዓመት ሴት ህይወት እንዳለፈ እና በሦስት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የሞስኮ ክልል አስተዳዳሪ አንድሬ ቮሮቢዮቭ ገለፁ። 🟠 የምዕራባውያን የጦር መሳሪያዎች አቅርቦትን የተመለከተ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ መስከረም 3 ቀን እንደሚካሄድ የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክትል ቋሚ ተወካይ ዲሚትሪ ፖሊያንስኪ ተናግሩ። 🟠 የእስራኤል አየር ሃይል በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ካን ዩኒስ በሚገኝ የሃማስ አዛዦች ዋና ፅህፈት ቤት ላይ ጥቃት ማድረሱን የሰራዊቱ የፕሬስ አገልግሎት ገለጸ። 🟠 ኪም ጆንግ ኡን ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር አቅሟን በከፍተኛ ደረጃ እንደምታሳድግ የሰሜን ኮሪያን 76ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ባደረጉት ንግግር ቃል ገብተዋል። 🟠 የሩሲያ ባህር ሃይል እስከ መስከረም 6 የሚቆየውን "ኦሺን-2024" ልምምዱን ጀመረ። የልምምዱ አላማ በሩሲያ እና በአጋር ሀገራት የባህር ኃይሎች መካከል ያለውን ትብብር ማስፋት እንደሆነ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። 🟠 በአርሜኒያ እና አዘርባጃን መካከል በተደረገው ረቂቅ የሰላም ስምምነት 13 አንቀጾች እና መቅድም ላይ ሙሉ በሙሉ ስምምነት እንደተደረሰ የአርመን ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሺንያን ተናግረዋል። 🟠 የ39 ዓመት እስራት የተፈረደበት አሜሪካዊው የፊልም ፕሮዲዩሰር ሃርቪ ዌይንስቲን በደረት ህመም ምክንያት ለልብ ቀዶ ጥገና ህክምና ኒውዮርክ በሚገኝ ሆስፒታል እንደገባ ተዘግቧል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የጳጉሜ 5 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦
የጳጉሜ 5 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦
Sputnik አፍሪካ
የጳጉሜ 5 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 በሞስኮ ክልል ራመንስኮዬ ከተማ በደረሰ የድሮንን ጥቃት የ46 ዓመት ሴት ህይወት እንዳለፈ እና በሦስት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የሞስኮ ክልል አስተዳዳሪ አንድሬ ቮሮቢዮቭ ገለፁ። 🟠 የምዕራባውያን የጦር... 10.09.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-09-10T11:43+0300
2024-09-10T11:43+0300
2024-09-10T12:04+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий