ቱርክ ብሪክስን ለመቀላቀል ያላት ፍላጎት አሜሪካን ስጋት ከቷታል ሲል አሜሪካው ጋዜጠኛ ሂንክል ተናገረ

ሰብስክራይብ
ቱርክ ብሪክስን ለመቀላቀል ያላት ፍላጎት አሜሪካን ስጋት ከቷታል ሲል አሜሪካው ጋዜጠኛ ሂንክል ተናገረየኔቶ ቁልፍ አባል የሆነችው ቱርክ የዩናይትድ ስቴትስ ጂኦፖለቲካል ባላንጣዎችን ሩሲያ እና ቻይናን ያቀፈውን ብሪክስን ለመቀላቀል መፈለጓ ዩናይትድ ስቴትስ ላይ ስጋት ፈጥሯል ሲል አሜሪካዊው ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ ተንታኝ ጃክሰን ሂንክል በምስራቃዊ ኢኮኖሚ ፎረም ጎን ለጎን ለስፑትኒክ ተናግሯል። "በጣም መጨነቅ ያለባቸው ይመስለኛል፤ ቱርክ ከአሜሪካ ውጪ በጣም አስፈላጊዋ የኔቶ አባል ነች ማለት ይቻላል።እናም አሁን ወደ ብሪክስ እንቀላቀል ወይስ በሚለው ጉዳይ ክርክር ላይ ናቸው። ህብረቱን ለመቀላቀል አመልክተዋል። በብሪክስ ስብሰባ ላይ እንደሚካፈሉ ተናግረዋል… ግን አሜሪካን በእርግጠኝነት ፈርታለች ሲል ሂንክል ተናግሯል።ሆኖም የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን ፖሊሲ መልቲ-ቬክተር ተፈጥሮን የተላበሰ በመሆኑ፤ በዚህ ረገድ እሱ ራሱ ሀገሪቱ ብሪክስ እንድትቀላቀል ይፈልጋል፤ ይህም ይሆናል ብሏል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0