በሀሰተኛ የትምህርት እና የስራ ልምድ በከፍተኛ "ኢንጅነር" ባለሙያነት ይሰራ የነበረው ግለሰብ በ15 አመት እስራት ተቀጣ

ሰብስክራይብ
በሀሰተኛ የትምህርት እና የስራ ልምድ በከፍተኛ "ኢንጅነር" ባለሙያነት ይሰራ የነበረው ግለሰብ በ15 አመት እስራት ተቀጣበደቡብ አፍሪካ የመንግስት የመንገደኞች ባቡር ኤጀንሲ ዋና መሀንዲስ የነበረው ዳንኤል ምቲምህሉ በኢንጂነሪንግ ሙያ የትምህረት ደረጃ እና ብቃት አለኝ በማለት ሲሰራ ቢቆይም በተደረገ ማጣራት ስለተደረሰበት በማጭበርበር ወንጀል የ15 አመት እስራት እንደተፈረደበት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በዓመት ወደ 2.8 ሚሊዮን ራንድ (ከ156.800 ዶላር በላይ) ያገኝ የነበረው ምቲምህሉ ዲግሪውን ከጀርመኑ ከዊትዋተርስራንድ ዩኒቨርሲቲ ያገኘ በማስመሰል መረጃ ያቀረበ ቢሆንም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ብቻ ማጠናቀቁ ተገልጿል።600 ሚሊዮን ዶላር (33.6 ሚሊዮን ዶላር) ራንድ የባቡር ድርድር ውድቅ በማድረግ ሂደት ግለሰብ ቁልፍ ሚና መጫወቱን ተከትሎ ይህ የማጭበርበር ተግባር ከ15 አመታት በኋላ በ2015 ተደርሶበታል። ፍርድ ቤቱ  የወንጀሉን ደረጃ አሳሳቢነት፣ የደረሰውን የገንዘብ ኪሳራ  በመጥቀስ በእምነትን ማጉደል ወንጀል ውሳኔ አሳልፏል። ቲምህሉ ይግባኝ ለማለት ማቀዱ ተዘግቧል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0