የነሐሴ 30 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡-

ሰብስክራይብ
የነሐሴ 30 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፡- 🟠 ቻይና የሁሉንም አካላት ጥቅም የሚያስጠብቅ ግልፅ እና ፍትሃዊ ዘመናዊ አሰራርን ለማበረታታት ከአፍሪካ መንግሥታት ጋር ተባብራ እንደምትሰራ ሺ ጂንፒንግ ገለፁ። 🟠 ደቡብ አፍሪካ የቡድን 20 ሊቀመንበርነቷን በመጠቀም ለግብር ማሻሻያ ድጋፍ በማድረግ ዓለም አቀፍ የሞኖፖል ድርጅቶች ገቢ በሚያገኙባቸው ሀገራት ግብር እንዲከፍሉ ለማረጋገጥ ድጋፍ እንደምታደርግ መንግሥት አስታውቋል። 🟠 የዩክሬን "ኦልካ" ሮኬት እና ሁለት ድሮኖች በቤልጎሮድ ክልል፣ ሶስት ድሮኖች በኩርስክ ክልል እንዲሁም ሁለት ተጨማሪ በብራያንስክ ክልል እንደወደሙ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ሪፖርት አድርጓል። 🟠 ፑቲን የተሳተፉበት የምስራቃዊ ኢኮኖሚ ፎረም ምልአተ ጉባኤ ዛሬ ተጀምሯል። 🟠 የዩክሬን ህጋዊ ስልጣን በ2014 በተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት እንደተቋረጠ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ፔስኮቭ ተናግረዋል። 🟠 ዩናይትድ ስቴትስ በ "ሮሲያ ሴጎድንያ" (የስፑትኒክ የበላይ ኩባንያ) ላይ ለጣለችው ማእቀብ ምላሽ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ተናግረዋል። 🟠 በርካታ የመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ሀገራት ለሩሲያ ቀላል ታክቲካል ተዋጊ ጄት ቼክሜት ፍላጎት እንዳሳዩ ተገልጿል። 🟠 የቴሌቭዥን ኩባንያው ኤቢሲ በትራምፕ እና ሃሪስ መካከል ለሚደረገው ክርክር ስራ ላይ የሚውለውን ደንብ አጠናቋል። 🟠 የ14 ዓመት ተማሪ በጆርጂያ ዩናይትድ ስቴትስ ትምህርት ቤት ተኩስ ከፈተ። ተኳሹ እንደተያዘ የገለጸው ኤፍቢአይ እንደ አዋቂ ሰው ጉዳዩ እንደሚታይ አስታውቋል። 🟠 ዛሬ ረቡዕ በመሬት ከባቢ አየር የተገኘው ተወርዋሪ አካል ፊሊፒንስ ውስጥ ታይቷል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0