የኢትዮጵያ መዲና ከንቲባ የመጀመሪያው ዘላቂ የከተሞች ልማት መድረክ አስፈላጊ እንደሆነ ተናገሩ ዘላቂ የከተሞች መስፋፋት ላይ ያተኮረው አህጉር አቀፍ መድረክ ትናንት ረቡዕ አዲስ አበባ በሚገኘው ታሪካዊው የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በይፋ ተጀምሯል። የአፍሪካ መሪዎች ከተሞቻቸውን ወደ ዘመናዊ የእድገትና ብልጽግና ማዕከላት ለማሸጋገር ትብብር እና ስትራቴጂ የሚቀይሱበት ወሳኝ መድረክ እንደሆነ ከንቲባዋ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል። በአፍሪካ ሀገራት መካከል እነዚህን ታላቅ አላማዎች ለማሳካት በትብብር መረባረብ እንዳለባቸው ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አጽንኦት በመስጠት ተናግረዋል። ፎረሙ አፍሪካውያን የጋራ ተግዳሮቶች እና እድሎች ላይ ትኩረት በመስጠት የሚወያዩበት ወሳኝ መድረክ እንደሆነም ጠቁመዋል። "በራሴና በከተማው አስተዳደር ስም ይህን እድል በመጠቀም የከተማችንን መስተንግዶ እና የባህል ሀብት እንድታሳዩ እጠይቃለሁ። እንግዶቻችንን ሞቅ ባለ አቀባበል በማስተናገድ ኢትዮጵያ የምትታወቅበትን ከበሬታ እና ቸርነት እናሳያቸው" ሲሉ ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ጽፈዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የኢትዮጵያ መዲና ከንቲባ የመጀመሪያው ዘላቂ የከተሞች ልማት መድረክ አስፈላጊ እንደሆነ ተናገሩ
የኢትዮጵያ መዲና ከንቲባ የመጀመሪያው ዘላቂ የከተሞች ልማት መድረክ አስፈላጊ እንደሆነ ተናገሩ
Sputnik አፍሪካ
የኢትዮጵያ መዲና ከንቲባ የመጀመሪያው ዘላቂ የከተሞች ልማት መድረክ አስፈላጊ እንደሆነ ተናገሩ ዘላቂ የከተሞች መስፋፋት ላይ ያተኮረው አህጉር አቀፍ መድረክ ትናንት ረቡዕ አዲስ አበባ በሚገኘው ታሪካዊው የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በይፋ ተጀምሯል።... 05.09.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-09-05T09:39+0300
2024-09-05T09:39+0300
2024-09-05T10:04+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የኢትዮጵያ መዲና ከንቲባ የመጀመሪያው ዘላቂ የከተሞች ልማት መድረክ አስፈላጊ እንደሆነ ተናገሩ
09:39 05.09.2024 (የተሻሻለ: 10:04 05.09.2024)
ሰብስክራይብ