የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የአቪዬሽን ዘርፉን ለማዘመን ትልቅ አላማ ያለው ፕሮግራም አስጀመረ የምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር በዓለም የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ቀዳሚ ተዋናይ ለመሆን ትልም በመያዝ በአቪዬሽን ዘርፍ ትልቅ የለውጥ እንቅስቃሴ ጀምራለች። የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ደኤታ ዴንጌ ቦሩ ማክሰኞ በተካሄደው የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ እንደተናገሩት የለውጥ ፕሮግራሙ እያደገ የመጣውን የአየር ትራንስፖርት ፍላጎት እና ከአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጋር የሚመጡ ፈተናዎችን ለመፍታት እና ደንቦችን ለማዳበር ያለመ ነው። በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ለመመስረት ያለውን ጠቀሜታ ግንዛቤ ውስጥ በመክተት የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ፕሮግራሙን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ደንጌ ቦሩ በአብክሮ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው መንግስቴ በበኩላቸው የትራንስፎርሜሽን ፕሮግራሙ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ማሳደግ፣ ለወደፊት ተግዳሮቶች የመቋቋም አቅምን ማጎልበት እንዲሁም ከአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጋር አብሮ መጓዝን ጨምሮ በርካታ ትልሞችን እንደሚያካትት ገልጸዋል። እንደ እርሳቸው ገለጻ በአየር ትራንስፖርት ልማት፣ ጥገና፣ እድሳት እና ምርመራ፣ የአየር መንገድ ልማት እና በግሉ ሴክተር ኢንቨስትመንት የኢትዮጵያን አቅም መጠቀምንም ይመለከታል። ባለድርሻ አካላት በንቃት በመሳተፍ ለፕሮግራሙ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ዋና ዳይሬክተሩ ጥሪ አቅርበዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የአቪዬሽን ዘርፉን ለማዘመን ትልቅ አላማ ያለው ፕሮግራም አስጀመረ
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የአቪዬሽን ዘርፉን ለማዘመን ትልቅ አላማ ያለው ፕሮግራም አስጀመረ
Sputnik አፍሪካ
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የአቪዬሽን ዘርፉን ለማዘመን ትልቅ አላማ ያለው ፕሮግራም አስጀመረ የምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር በዓለም የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ቀዳሚ ተዋናይ ለመሆን ትልም በመያዝ በአቪዬሽን ዘርፍ ትልቅ የለውጥ እንቅስቃሴ ጀምራለች።... 04.09.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-09-04T19:06+0300
2024-09-04T19:06+0300
2024-09-04T19:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የአቪዬሽን ዘርፉን ለማዘመን ትልቅ አላማ ያለው ፕሮግራም አስጀመረ
19:06 04.09.2024 (የተሻሻለ: 19:44 04.09.2024)
ሰብስክራይብ