የዲጂታል ደኅንነት ኢትዮጵያን ለማዘመን እና ብሔራዊ ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ ወሳኝ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገሩ ይፋዊ ቁልፍ መሰረተ ልማት ስርዓትን(PKI) ባስጀመሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር የዲጂታል ልማትን ለመደገፍ ጠንካራ የቨርቹዋል ሴኪዩሪቲ ሲስተም አስፈላጊ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አንስተዋል። ሀርድዌር፣ ሶፍትዌር፣ ባለሙያዎችን እና የህግ ማእቀፍን የያዘው ቁልፍ የመሰረተ ልማት ስርዓት ሂሳባዊ ቀመርን በመጠቀም መረጃን መመስጠር እንዲሁም ላኪና ተቀባይ ብቻ በሚያውቁት ሚስጢራዊ ቁልፍ የተመሰጠረን መረጃ መፍታት ላይ እንደሚሰራ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። በተጨማሪም በዲጂታል ሰርቲፊኬት አገልግሎት አማካኝነት ዲጂታል ፊርማ እና የመረጃን ሚስጥራዊነት ማረጋገጥ ያስችላል። ወታደራዊ ጥንካሬ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የነበረውን ታሪካዊ ጉልህ ሚና ያነሱት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የሳይበር ጥቃት በአሁኑ ሰዓት እያስከተለ ያለውን ስጋት ጠቁመዋል። እነዚህን ስጋቶች ለመከላከል እና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በዚህ የዲጂታል ዘመን ለማጠናከር አዲሱ የፒኬአይ ስርዓት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ እና ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዲጂታል ጉዞ የበለጠ እንደሚያፋጥን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የዲጂታል ደኅንነት ኢትዮጵያን ለማዘመን እና ብሔራዊ ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ ወሳኝ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገሩ
የዲጂታል ደኅንነት ኢትዮጵያን ለማዘመን እና ብሔራዊ ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ ወሳኝ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገሩ
Sputnik አፍሪካ
የዲጂታል ደኅንነት ኢትዮጵያን ለማዘመን እና ብሔራዊ ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ ወሳኝ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገሩ ይፋዊ ቁልፍ መሰረተ ልማት ስርዓትን(PKI) ባስጀመሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር የዲጂታል ልማትን ለመደገፍ ጠንካራ የቨርቹዋል ሴኪዩሪቲ... 03.09.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-09-03T14:22+0300
2024-09-03T14:22+0300
2024-09-03T14:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የዲጂታል ደኅንነት ኢትዮጵያን ለማዘመን እና ብሔራዊ ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ ወሳኝ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገሩ
14:22 03.09.2024 (የተሻሻለ: 14:44 03.09.2024)
ሰብስክራይብ