የላይቤሪያ መርከብ የፓናማ ቦይን በመሻገር ትልቁ የጭነት አጓጓዥ ሆነ 17,640 ኮንቴይነሮች ጭኖ በቦዩ አርብ እለት እንደተላለፈ የተገለጸው የላይቤሪያ ባንዲራ አውለብላቢ የንግድ መርከብ በ110 ዓመታት የስራ ጊዜ ውስጥ በፓናማ ካናል የተላለፈ ትልቁ መርከብ በመሆን ሪከርድ መስበር እንደቻለ የፓናማ ካናል ባለስልጣን አስታውቋል። 366 ሜትር እርዝመት እና 51 ሜትር ስፋት ያለው ኤምኤስሲ ሜሪ የኮንቴይነር መርከብ ከሜክሲኮ ፓሲፊክ ማንዛኒሎ ወደብ በፓናማ ካሪቢያን የባህር ዳርቻ ወደሚገኘው ወደብ አቋርጧል። መርከቡ በመተላለፊያው ለማለፍ ከ1.3 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከፍሏል ተብሏል። በ2023 17,312 ኮንቴይነሮችን በመያዝ ቦዩን አቋርጦ የነበረው ኤቨር ማክስ መርከብ ሪከርዱን ይዞ መቆየቱን የፓናማ ካናል ባለስልጣን መግለጫ አመልክቷል። የፓናማ ቦይ እ.አ.አ. ነሐሴ 15፣ 1914 ነበር በዩናይትድ ስቴትስ የተከፈተው። ይህ የ50 ማይል (80 ኪሎ ሜትር) ቦይ ከተከፈተበት ጊዜ ጀምሮ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ መርከቦች ተላልፈውበታል። የውሃ መተላለፊያው ትላልቅ እና ጥልቀት ያላቸው መርከቦች እንዲያልፉ ለማስቻል በ2016 ማስፋፊያ ተደርጎለታል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የላይቤሪያ መርከብ የፓናማ ቦይን በመሻገር ትልቁ የጭነት አጓጓዥ ሆነ
የላይቤሪያ መርከብ የፓናማ ቦይን በመሻገር ትልቁ የጭነት አጓጓዥ ሆነ
Sputnik አፍሪካ
የላይቤሪያ መርከብ የፓናማ ቦይን በመሻገር ትልቁ የጭነት አጓጓዥ ሆነ 17,640 ኮንቴይነሮች ጭኖ በቦዩ አርብ እለት እንደተላለፈ የተገለጸው የላይቤሪያ ባንዲራ አውለብላቢ የንግድ መርከብ በ110 ዓመታት የስራ ጊዜ ውስጥ በፓናማ ካናል የተላለፈ ትልቁ... 02.09.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-09-02T10:42+0300
2024-09-02T10:42+0300
2024-09-02T11:04+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий