የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን ያለውን ረሃብ ለመዋጋት የሚያስችል 7 ሚሊዮን ዶላር መድባለችየተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ከዩኒሴፍ ጋር በመሆን በሁለቱ የአፍሪካ ሀገራት ለተከሰተው የረሃብ ቀውስ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ ለማድረስ ስምምነት ተፈራርመዋል። ከዚህ ገንዘብ ውስጥ 6 ሚሊዮን ዶላሩ ለሱዳን እንዲሁም 1 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ ለደቡብ ሱዳን የሚውል ይሆናል።በሱዳን 17.7 ሚሊየን ህዝብ በደቡብ ሱዳን ደግሞ 7.1 ሚሊዮን ህዝብ በምግብ እጦት እየተሰቃየ መሆኑ ተጠቅሷል።ቀደም ሲል የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ሱዳንን እና ጎረቤት ሀገራትን ለመደገፍ በሚያዝያ ወር በተካሄደው አለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ቃል ከገባችው 100 ሚሊየን ዶላር ውስጥ 70 በመቶውን የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች።እ.አ.አ ከሚያዝያ 15 ቀን 2023 ጀምሮ በሱዳን መደበኛው ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ሃይል (አርኤፍኤ) መካከል ከባድ ጦርነት ሲካሄድ ቆይቷል። የመንግስታቱ ድርጅት እንደገለጸው በሱዳን ከ8.2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በግጭቱ ምክንያት ቤታቸውን ጥለው ተሰደዋል፣ ከእነዚህም መካከል 1.7 ሚሊዮን ገደማ በአጎራባች ሀገራት የተጠለሉ ናቸው።ከዚህም በላይ በሀገሪቱ በተከሰተው ግጭት ከ13,000 በላይ ሰዎች መሞታቸውንና ከ30,000 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን ያለውን ረሃብ ለመዋጋት የሚያስችል 7 ሚሊዮን ዶላር መድባለች
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን ያለውን ረሃብ ለመዋጋት የሚያስችል 7 ሚሊዮን ዶላር መድባለች
Sputnik አፍሪካ
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን ያለውን ረሃብ ለመዋጋት የሚያስችል 7 ሚሊዮን ዶላር መድባለችየተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ከዩኒሴፍ ጋር በመሆን በሁለቱ የአፍሪካ ሀገራት ለተከሰተው የረሃብ ቀውስ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ ለማድረስ... 01.09.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-09-01T12:02+0300
2024-09-01T12:02+0300
2024-09-01T14:04+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን ያለውን ረሃብ ለመዋጋት የሚያስችል 7 ሚሊዮን ዶላር መድባለች
12:02 01.09.2024 (የተሻሻለ: 14:04 01.09.2024)
ሰብስክራይብ