የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ከፍተኛ የጦር መኮንኖችን አባረሩ

ሰብስክራይብ
የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ከፍተኛ የጦር መኮንኖችን አባረሩ🪖 ፕሬዝዳንቱ አርብ ዕለት በሀገሪቱ ጦር ኃይሎት ውስጥ ዲሲፕሊን የሌላቸውን የሰራዊት አመራር እና አባላትን ለማፅዳት በማለም ፤ ሜጄር ጄኔራል ማርቲን ንዛራምባ እና ኮሎኔል ኢቲን ኡዊማን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችን አሰናብተዋል።ሌሎች 195 ወታደራዊ አባላትን ጨምሮ  ከስራ የተባረሩት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች፤ በሙስና፣ በሥነ ምግባር ጉድለት እና በወታደራዊ ስነ ምግባር ጥሰት ክስ የተመሰረተባቸው መሆኑን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።የሩዋንዳ መከላከያ ሃይል በጦር ሠራዊቱ ውስጥ ጥብቅ ዲሲፕሊን ማስፈጸሙን ቀጥሏል፣ ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ እርምጃ ሲወሰድ ቆይቷል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0