የነሀሴ 30 ረፋድ ዋና ዋና የአለም ዜናዎች

ሰብስክራይብ
የነሀሴ 30 ረፋድ ዋና ዋና የአለም ዜናዎች🟠 ደቡብ አፍሪካ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ አቅም ለማሳደግ ያለመ ማሻሻያ እያደረገች ነው ያሉት የማዕከላዊ ባንክ ኃላፊ፣ የሀይል እጥረት ቀውሱን በተሳካ ሁኔታ መወጣት መቻላችን በሌሎች ዘርፎች እድገትን ሊያመጣ ይችላል ብለዋል።🟠 የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ፕሪቶሪያ በጋዛ ሰርጥ ፍልስጤማውያን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን እና እየተፈጸመ መሆኑን ለማረጋገጥ ጠንከር ያለ መከራከሪያዎች በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንደሚያቀርቡ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።🟠  የናይጄሪያ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም በኒያሚ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ኒጀር እና ናይጄሪያ በጸጥታ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ስምምነት ላይ ደርሰዋል።🟠የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በአንድ ጀምበር 18 የዩክሬን ድሮኖችን ማውደሙን አስታውቋል። 11 በብራያንስክ ክልል፣ 4 በካሉጋ ክልል    2 በክራይሚያ እና 1 በቤልጎሮድ ክልል የወደሙ ናቸው።🟠 ፑቲን ለቤላሩሱን ፕሬዝዳንት የቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ የመጀመሪያ ጥሪ የተሰኘውን ከፍተኛውን የሀገሪቱን ሽልማት ሰጡ።🟠  ማክሮን የዱሮቭን ፈረንሳይ መምጣት እንደማያውቁ እና ከእሱ ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ እንዳልነበራቸው ተናግረዋል።🟠  የአለም አቀፉ አውቶሚክ ኢነርጂ (IAEA)ዋና ዳይሬክተር በሚቀጥለው ሳምንት በዛፖሮዚያ ከሚያደርጉት ጉብኝት አስቀድሞ በዛፖሮዚያ የኑክሌር ሃይል ማመንጫ ጣቢያ የኒውክሌር አደጋን ማስወገድ አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።🟠 የአሜሪካ ሁኔታዎችን የማባባስ ጉ ዳይ ፀብ አጫሪ እየሆነ መጥቷል ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት ማሪያ ዛካሮቫ ተናገረዋል። አክለውም ዩናይትድ ስቴትስ ኪየቭ የሩሲያን ድንበር ዘልቃ መምታት እንድትችል ጭምር ማንኛውንም የጦር መሳሪያ መጠቀም እንድትችል ለኪየቭን ለመስጠት በዝግጅት ላይ ነች ብለዋል። 🟠  ዶናልድ ትራምፕ የኒውክሌር ጦር መሳሪያን ለአሜሪካም ሆነ ለአለም እንደ ዋና ችግር እንደሚቆጥሩ ገልፀው መቼም ጥቅም ላይ እንዳይውል ማድረግ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።🟠 የኒውዚላንድ ማኦሪ ንጉስ ቱሄቲያ ፓኪ ቴ ዊሮሄሮ ሰባተኛ በ69 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።🟠 በካምቻትካ የባህር ዳርቻ 6.1 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል ሲል የሩሲያ የሳይንስ አካዳሚ የጂኦፊዚካል አገልግሎት አካዳሚ ቅርንጫፍ ገለፀ።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0