ደቡብ አፍሪካዊው ጀሃን ሩፐርት አሊኮ ዳንጎቴን በመብለጥ ቀዳሚ የአፍሪካ ባለጸጋ መሆኑን የብሉምበርግ ቢሊየነሮች መረጃ ጠቋሚ አስታወቀ

ሰብስክራይብ
ደቡብ አፍሪካዊው ጀሃን ሩፐርት አሊኮ ዳንጎቴን በመብለጥ ቀዳሚ የአፍሪካ ባለጸጋ መሆኑን የብሉምበርግ ቢሊየነሮች መረጃ ጠቋሚ አስታወቀየደቡብ አፍሪካዊው ቢሊየነር ሀብት በዚህ አመት በ1.87 ቢሊዮን ዶላር ሲያድግ የዳንጎቴ ሀብት ግን በ1.7 ቢሊዮን ዶላር ቀንሷል።ሩፐርት የቅንጦት ሰዓት ሰሪ ሪችሞንት ባለቤት ሲሆን እንደ ካርቲየር እና ጄገር - ሌኮልተር  ያሉ ብራንዶች ባለቤት ነው። በተጨማሪም በኢንቨስትመንት ድርጅቱ ሬምግሮ በኩል ከ30 በላይ ኩባንያዎች ውስጥ ድርሻ አለው።የዳንጎቴ ሀብት በዋናነት በዳንጎቴ ሲሚንቶ ያለው የ86 በመቶ ድርሻ ሲሆን በዳንጎቴ ስኳር፣ ናስኮን አጋር ኢንዱስትሪዎች፣ ዩናይትድ ባንክ አፍሪካ እና በሌጎስ የሚገኘው የዳንጎቴ ነዳጅ ማጣሪያ አክሲዮን ባለቤት ነው።ሌሎች ከፍተኛ የአፍሪካ ቢሊየነሮች ኒኪ ኦፔንሃይመር (11.3 ቢሊዮን ዶላር)፣ ናሴፍ ሳዊሪስ (9.37 ቢሊዮን ዶላር) እና ናቲ ኪርሽ (9.14 ቢሊዮን ዶላር) ሀብት በማካባት ይመራሉ።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0