የነሐሴ 22 ምሽት ዋና ዋና ዓለም አቀፍ ዜናዎች፡-

ሰብስክራይብ
የነሐሴ 22 ምሽት ዋና ዋና ዓለም አቀፍ ዜናዎች፡- 🟠 የተመድ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሱዳን የሚገኙ ሁለት ተወካዮቹን በማጭበርበር እና መረጃን በመደበቅ ጠርጥሮ ምርመራ መጀመሩን መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። 🟠 የኒጀር እና ናይጄሪያ ጦር ኃይል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሞች በኒጀር ዋና ከተማ ኒያሜ ውይይት አካሄዱ። 🟠 የናይጄሪያ መንግሥት በሽብር ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች እና ድርጅቶችን አጠቃላይ ዝርዝር ይፋ ለማድረግ ማቀዱን አስታወቀ። 🟠 ፓቬል ዱሮቭ ክስ እንዲመሰረትበት ሊወስን ይችላል በተባለ የምርመራ ዳኛ ፊት ቀርበ። የፈረንሳይ አቃቤ ህግ ቢሮ የዱሮቭን ጉዳይ በተመለከተ ዛሬ ምሽት መግለጫ እንደሚሰጥ ምንጮች ለስፑትኒክ ተናግረዋል። 🟠 የሩሲያ ዲፕሎማቶች የዱሮቭን ጉዳይ በተመለከተ አስፈላጊውን ሁሉ እያደረጉ ነው ሲሉ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ተናግረዋል። 🟠 የኪዬቭ አገዛዝ በኩርስክ ክልል በፈጸመው የሽብር ጥቃት ሳቢያ ከዩክሬን ጋር ምንም አይነት ድርድር ሊኖር እንደማይችል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይዋ አስታውቀዋል። 🟠 የባይደን አማካሪ ሱሊቫን ቻይናን በጎበኙበት ወቅት ቤጂንግ ለሩስያ የመከላከያ ኢንዱስትሪ የምታደርገውን ድጋፍ አስመልክቶ “ስጋታቸውን ገልጸዋል” ሲል ዋይት ሀውስ ተናገረ። 🟠 የዩክሬን የውሃ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች ከየካቲት 2022 ጀምሮ የማመንጨት አቅማቸው ከ40% በላይ እንደቀነሰ እና በሀገሪቱ አንድም ያልተጎዳ የውሃ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ እንደማይገኝ የዩክሬን የመንግሥት ኩባንያ ኡክሪድሮኔርጎ አስታወቀ። 🟠 ስዊዘርላንድ ከ2018 ጀምሮ አዳዲስ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች ግንባታ ላይ ተጥሎ የነበረውን እገዳ ለማንሳት ማቀዷን የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0